Sunday, September 22, 2024
spot_img

የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ከታጣቂ ቡድን ጋር ያደረገውን ስምምነት ችግሩን የሚያባብስና ሕገ ወጥ ነው ተባለ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ግንቦት 16፣ 2013 ― የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል መንግሥት ባሳለፍነው ግንቦት 10፣ 2013 በክልሉ በሕገ ወጥ መንገድ ከሚንቀሳቀሰው ታጣቂ ቡድን ጋር በጋራ ለመሥራት መስማማቱ የዜጎችን ችግር የሚያባብስና ሕገ ወጥ ስምምነት መሆኑን በክልሉ የሚንቀሳቀሰው ቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ አስታውቋል፡፡

የክልሉ መንግሥት ከታጣቂ ቡድኑ ተወካዮች ጋር ያደረገው ስምምነት በእጅጉ የሚያስደነግጥና ወደፊት በአካባቢው የሚፈጠረውን ችግር ለመገመት የሚከብድ እንደሚያደርገው የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ መብራቱ አለሙ ገልጸዋል።

አቶ መብራቱ እንደገለጹት ከሆነ፣ የስምምነት ሰነዱ ለታጣቂው ኃይል በወረዳ፣ በዞንና በክልል ደረጃ ስልጣን ለማጋራት እና የታጣቂው ኃይል አባላትን በክልሉ የጸጥታ መዋቅር ለማካተት የተፈረመ መሆኑን ጠቁመዋል።

“በኢትዮጵያ ሕግ መሰረት የኃላፊነት ቦታን መያዝ የሚቻለው በምርጫ ብቻ መሆኑ እየታወቀ፣ ነገር ግን የኃይል አማራጭ ተጠቅሞ ጫካ ገብቶ ሕዝብ ከጨፈጨፈ ኃይል ጋር ስልጣን ለማጋራት መስማማት እጅግ በጣም አስገራሚ ታሪካዊ ስህተት ነው” ብለዋል፡፡ ፓርቲው አካባቢውን በንቃት እንደሚከታተል የጠቆሙት አቶ መብራቱ፣ ስምምነቱ የክልሉን ህዝብ ፍላጎት ያማከለ እንዳልሆነ እና የግለሰብ ውሳኔ ላይ የተንጠለጠለ ነው የሚል አቋም እንዳላቸው መግለጻቸውን አዲስ ማለዳ ዘግቧል፡፡

አዲስ ማለዳ የታጣቂው ኃይል ሰለባ ሆነው የተፈናቀሉ ዜጎችን አነጋግሬ ስምምነቱ ችግራቸውን ከማባባስ በዘለለ ለውጥ እንደማያመጣ ነግረውኛል ብሏል። ለዚህም እንደ ማሳያት የሚያነሱት ከዚህ በፊት የታጣቂው ኃይል አባላት ተስማምተናል ብለው የተሃድሶ ስልጠና ወሰዱ ተብሎ በነበረበት ወቅት የቦታውን መውጫ መግቢያ አጥንተው መልሰው ከድተው ጥቃት እንዳደረሱባቸው አስታውሰዋል።

የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል መንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ እንዳስታወቀው ከሆነ፣ ከታጣቂ ቡድኑ ጋር በተስማሙበት የስምምነት ሰነድ ውስጥ ከታጣቂ ሃይል አባላት መካከል አቅምና የትምህርት ደረጃቸውን በማየት በክልል ደረጃ 2 ፣ በዞን ደረጃ 3 እና በወረዳ ደረጃ ደግሞ 4 የኃላፊነት ቦታ እንዲያገኙ ማድረግ፣ የከተማ የቤት መስሪያ ቦታ፣ የገጠር የእርሻ መሬት እንዲያገኙ ማድረግ፣ ሴቶችን በማካተት በተለያዩ ማህበራት እንዲደራጁ ማስቻል፣ በተማሩበት የሙያ መስክ እንዲመደቡ ማድረግ፣ ከአሁን በፊት ልምድ ያላቸውን ሰዎች በክልሉ ውስጥ ባሉ የጸጥታ መዋቅሮች መመደብ እና የብድር አገልግሎት መስጠትን የመሳሰሉ ሀሳቦች ይገኙበታል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img