Tuesday, October 8, 2024
spot_img

ሰበር ዜና የሚኒስትሮች ምክር ቤት ለግሎባል ፓርትነርሺፕ ፎር ኢትዮጵያ የቴሌኮም ፈቃድ እንዲሰጥ ወሰነ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ግንቦት 14፣ 2013 ― የሚኒስትሮች ምክር ቤት ለግሎባል ፓርትነርሺፕ ፎር ኢትዮጵያ የቴሌኮም ፈቃድ እንዲሰጥ ወወሰኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታውቀዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ‹‹ከፍተኛ የፈቃድ ክፍያ ዋጋ እና አስተማማኝ የሙዓለ ነዋይ ፍሰት ዕቅድ›› አቅርቧል ላሉት ግሎባል ፓርትነርሺፕ ፎር ኢትዮጵያ የኢትዮጵያ የኮሙኒኬሽን ባለሥልጣን አዲስ ሀገር አቀፍ የቴሌኮም ፈቃድ እንዲሰጥ በአንድ ድምፅ ማጽቁን ነው የገለጹት፡፡

ኢትዮጵያን ሙሉ ለሙሉ ወደ ዲጂታል አገልግሎት የማስገባት ዕቅዳችን ፈር ይዟል ያሉት እንደ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ ‹‹ይህን ግልጽነት እና ውጤታማነት የሞላበት ሂደት ላሳካችሁ ሁሉ ምስጋናዬ ይድረስ›› ሲሉ አስፍረዋል፡፡

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ፈቃድ እንዲሰጠው የወሰነለት ግሎባል ፓርትነርሺፕ ፎር ኢትዮጵያ ቮዳፎን፣ ቮዳኮም እና ሳፋሪኮም የተባሉት እህትማማች ድርጅቶችን የያዘ ነው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img