Sunday, October 6, 2024
spot_img

ምርጫ ቦርድ የመራጮች ምዝገባ ዘግይቶ በጀመረባቸው የወለጋ ዞኖች ምዝገባ መጠናቀቁን አስታወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ግንቦት 14፣ 2013 ― የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለስድስተኛው አገራዊ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ ዘግይተው የጀመሩት የምእራብ ወለጋ፣ የምሥራቅ ወለጋ፣ የሆሮጉድሩ ወለጋ እና የቄለም ወለጋ ዞኖች ምርጫ ክልሎች ሲያከናውን የነበረው ምዝገባ በትላንትናው እለት መጠናቀቁን አስታውቋል፡፡

ቦርዱ በነዚህ አካባቢዎች ምዝገባ ካካሄደባው 24 የምርጫ ክልሎች በተጨማሪ በሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች ማለትም በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሽ ዞን ሲከናወን የነበረው ምዝገባ እና የአማራ ክልል ኦሮሞ ብሔር ልዩ ዞን የሚገኙት ዳዋ ጨፌ፣ ጨፋ ሮቢት እና ባቲ ምርጫ ክልሎች በተመሳሳይ ሁኔታ የምርቸቻ ምዝገበው ተጠናቋል ብሏል፡፡

በነዚህ ምርጫ ክልሎች የመራጮች መዝገብ ለሚቀጥሉት 10 ቀናት ማለትም እስከ ግንቦት 23፣ 2013 ድረስ ለሕዝብ ይፋ ይደረጋል ያለው ቦርዱ፣ የመራጮች ምዝገባ ቀን ከተጠናቀቀበት ቀን በኋላ ምንም አይነት ምዝገባ ማካሄድ እንደማይቻልም ነው የገለጸው፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከሁለት ሳምንት በፊት ይፋ ባደረገው አሃዝ መሠረት በመላ አገሪቱ ለምርጫው የተመዘገቡት ሰዎች ብዛት ከ31 ሚሊዮን መድረሱን አሳውቆ ነበር፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img