Sunday, October 6, 2024
spot_img

ሱዳን እና ግብጽ የጋራ ወታደራዊ ልምምድ ሊያደርጉ ነው

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ግንቦት 14፣ 2013 ― ሱዳን እና ግብጽ የናይል ወንዝ ስጋቶችን መጠበቅ ዓላማው ያደረገ የጋራ ወታደራዊ ልምምድ ሊያደርጉ መሆኑን አስታወቁ።

የሱዳን ወታደራዊ ሚዲያ ባወጣው መግለጫ የናይል ወንዝ ስጋቶችን ማስወገድ ዓላማው ያደረገ የጦር ልምምድ የሚደረገው የፊታችን ግንቦት 18 አንስቶ እስከ ግንቦት 23፣ 2013 ነው፡፡ በጋራ የጦር ልምምዱ የግብጽ እና ሱዳን ወታደሮች ይሳተፋሉ የተባለ ሲሆን፣ በልምምዱ ላይ ከእግረኛ ጀምሮ በሁሉም ክፍል የሚገኙ ወታደሮች እንደሚሳተፉ መግለጫው አክሏል።

በሱዳን መሬት ላይ በሚካሄደው የጋራ ጦር ልምምድ የግብጽ ጦር በካርቱም የአየር ጦር ማዘዣ ከነ መለማመጃ መሳሪያው መግባቱም ተጠቁሟል።

‹‹የናይል ዘብ 1 እና 2›› የሚል ሥያሜ ያለው ይህ ወታደራዊ የጦር ልምምድ በናይል ወንዝ ላይ ወታደራዊ ትብብሮችን፤ ልምድ መለዋወጥ እና ሌሎች ጥቅሞችን ማግኘት ዋና አላማው ነው ተብሏል። ሱዳን እና ግብጽ ባሳለፍነው ሚያዝያ በሰሜናዊ ሱዳን ግዛት ተመሳሳይ የጋራ ጦር ልምምድ ማድረጋቸው ይታወሳል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img