Sunday, October 6, 2024
spot_img

የኤርትራ ወታደሮች በአክሱም 110 ንጹሐን ሰዎች መግደላቸውን ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አስታወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ግንቦት 14፣ 2013 ― በትግራይ ክልል አክሱም ከተማ ኅዳር 19 እና 20፣ 2013 በነበረው ውጊያ የኤርትራ ወታደሮች 110 ንጹሐን ሰዎች መግደላቸውን የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ባወጣው የምርመራ ሪፖርት አስታውቋል፡፡

ዐቃቤ ሕግ በትናትናው እለት በትግራይ ክልል እያካሄደ ያለውን ምርመራ አስመልክቶ ባወጣው መግለጫው በትግራይ ክልል አክሱም ከተማ ህዳር 2013 ተፈጽመዋል የተባሉ ወንጀሎች ላይ የምርመራ ሥራ መቀጠሉን ገልጧል፡፡

በምርመራው መሠረት 70 ሰዎች በአክሱም ከተማ ውስጥ በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ መንገድ ላይ እያሉ መገደላቸውን ያመላከተው ምረመራው፤ ከሟቾቹ ውስጥ ወታደራዊ የደንብ ልብስ ባይለብሱም በጦርነቱ የተሳተፉ ሰዎች መኖራቸው መረጋገጡን አስታውቋል።

በሌላ መልኩ 40 ንጹሃን ሰዎች ደግሞ የኤርትራ ወታደሮች ቤት ለቤት ባደረጉት አሰሰሳ ከቤታቸው እንዲወጡ ተደርገው እና በቤታቸው ውስጥ መገደላቸውንም ምርመራው አመላክቷል።

ከዚህ በተጨማሪ በከተማዋ በርከት ያሉ የንብረት ዘረፋ እና ውድመት መድረሱን ያመላከተው ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ሪፖርት፤ ከእነዚም ውስጥ የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ካምፓሶች፣ ቅድስት ማርያም ሆስፒታል ብራና ሆቴል ይገኙበታልም ብሏል።

በወቅቱ በአክሱም በነበረው ውጊያ የደረሰውን ጉዳት ለማጣራት 119 ሰዎች የምስክርነት ቃል እንዲሰጡ መደረጉን፣ የሕክምና ማስረጃዎች፣ የፎቶ እና ቪዲዮ ማስረጃዎችን ማሰባሰቡንም ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በሪፖርቱ መግለጹን የዘገበው አል ዓይን ነው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img