Monday, September 23, 2024
spot_img

የካናዳ መንግሥት በኢትዮጵያ ለተራድኦ ሠራተኞች ከለላ እንዲደረግ የሚጠይቀውን የአሜሪካ ጥሪ ተቀላቀለ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ግንቦት 14፣ 2013 ― የካናዳ መንግሥት አሜሪካ ከትላንት በስትያ ግንቦት 12 በተያዘው ዓመት በኢትዮጵያ ስምንት የተራድኦ ሠራተኞች መገደላቸውን በመግለጽ ለሠራተኞቹ ከለላ እንዲደረግላቸው በሚል ያቀረበችውን ጥሪ ተቀላቅሏል፡፡

በውጭ ጉዳይ ግንኙነቱ የአሜሪካን አቋም የሚያራምደው የካናዳ መንግሥት ከዚህ ቀደም በተመሳሳ በትግራይ ክልል የተፈጠሩ ችግሮችን አስመልክቶ በተመሳሳይ የአሜሪካን አቋም ሲደግፍ የቆየ ነው፡፡

የተራድኦ ሠራተኞቹን አስመልክቶ በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ባወጣው መግለጫ እንዳመለከተው ከኅዳር ወር ወዲህ ባለው ጊዜ ውስጥ ከተገደሉት የረድኤት ተቋማት ሠራተኞች ሰባቱ ግጭት ባጋጠመበት በትግራይ ክልል ውስጥ መሞታቸው ሲታወቅ፣ አንደኛው ግን በሌላ የአገሪቱ ክፍል ውስጥ መገደሉን ገልጿል።

የተገደሉት የእርዳታ ሠራተኞች ለችግር የተጋለጡ ሰዎችን ለመደገፍ ሥራቸውን በማከናወን ላይ ሳሉ መሆኑን የኤምባሲው መግለጫ አመልክቶ፤ ድርጊቱን አጥብቆ አውግዞታል። እንዲህ አይነቱ ጥቃት እንዲቆም የጠየቀ ሲሆን ተጠያቂዎቹም ለፍርድ እንዲቀርቡ ጠይቋል።

በዚህም የአሜሪካ መንግሥት በአገሪቱ ውስጥ ያሉ ሁሉም የታጠቁ ኃይሎች ለረድኤት ድርጅቶች ሠራተኞች ህይወት እና ሥራ ጥበቃ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል።

መግለጫው ጨምሮም የኢትዮጵያ መንግሥት የእርዳታ ሥራ የሚያከናውኑ ሠራተኞችን ጨምሮ የሰላማዊ ሰዎችን ደኅንነት የመጠበቅ ዋነኛ ሚናው መሆኑን ጠቅሶ፤ የታጠቁ ኃይሎችም በዓለም አቀፍ የሰብአዊ አቅርቦት ሕግ መሠረት ግዴታቸውን እንዲወጡ ጠይቋል፡፡ ሁሉም የታጠቁ ኃይሎች የረድኤት ሠራተኞችና የሚያቀርቡት እርዳታ ደኅንነት ተጠብቆ ሳይገደብ፣ ዘላቂነት ባለው ሁኔታ ድጋፍ ለሚፈልጉ ለሁሉም ሰዎች እንዲደርስ እንዲያደርጉ ጠይቋል።

መግለጫው በማጠቃለያው ላይ የኢትዮጵያ መንግሥት በአስቸኳይ በእርዳታ ሠራተኞችና በሰላማዊ ሰዎች ላይ የተፈጸሙ ግድያዎቹን እንዲያወግዝና ምርመራ በማድረግ አጥፊዎችን ተጠያቂ እንዲያደርግ አጥብቆ ጠይቋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img