Saturday, November 23, 2024
spot_img

የአሜሪካ መንግሥት በመላ ኢትዮጵያ ለሚገኙ የረድኤት ሠራተኞች ጥበቃ እንዲደረግ ጠየቀ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ግንቦት 12፣ 2013 ― የአሜሪካ መንግሥት በመላው ኢትዮጵያ ለሚገኙ የተራድኦ ሠራተኞች የታጠቁ አካላት ጥበቃ እንዲያደርጉ ጠይቋል።

የአገሪቱ መንግሥት በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ድረ ገጽ ላይ ባስነበበው መግለጫው፣ ይህንኑ ተግባር የመከወን ቀዳሚ ኃላፊነት የኢትዮጵያ መንግሥት መሆኑን ያመለከተ ሲሆን፣ ሌሎች ታጣቂ ኃይሎችም በዓለም አቀፍ ሕግጋት መሠረት ግዴታቸውን ሊወጡ ይገባል ብሏል።

ከኅዳር ወር አንስቶ በትግራይ ክልል ብቻ ሰባት፣ በሌላ የአገሪቱ አካባቢ ደግሞ አንድ የተራድኦ ሠራተኞች መገደላቸውንም የገለፀው የአሜሪካ መንግሥት፣ በቅርብ ጊዜ በቆላ ተምቤን የተገደለው የዩኤስአይዲ ባልደረባ መሆኑንም ጠቅሷል።

የሠራተኞቹን ግድያ የኮነነው የአሜሪካ መንግሥት፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ግድያውን የፈጸሙ አካላትን በአስቸኳይ ለሕግ እንዲያቀርቡ ጠይቋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img