Sunday, September 22, 2024
spot_img

መሐመድ ዴክሲሶ አዲስ አበባ እንደሚገኝ ተነገረ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ግንቦት 12፣ 2013 ― በየካቲት ወር በጂማ ዩኒቨርሲቲ በነበረ የምርቃት ሥነ ሥርዐት ላይ ጃዋር መሐመድ ይፈታ እና ፍትሕ ለሐጫሉ የሚል መፈክር አሰምቶ በቀጥጥር ስር የዋለው መሐመድ ዴክሲሶ አዲስ አበባ እንደሚገኝ ወንድሙ ሡልጣን ዴክሲሶ መናገሩን አዲስ ስታንዳርድ አስነብቧል።

የመሐመድ ወንድም በአሁኑ ወቅት አዲስ አበባ እንደሚገኝ ቢናገርም፣ ቀድሞ የት እንደነበር እንደማያውቅ ነው የገለጸው።

ወንድምየው ጨምሮም መሐመድ ወደ አዲስ አበባ የመጣው በኦሮሚያ ልዩ ኃይል መሆኑን መረዳቱን የገለጸ ሲሆን፣ ለማግኘት ያደረገው ሙከራ ግን ወደ ገላን ተወስዷል በመባሉ አለመሳካቱን ጠቁሟል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img