Sunday, October 6, 2024
spot_img

ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች ቡድን መንግሥት የኒውዮርክ ታይምስ ዘጋቢን ፍቃድ እንዲመልስለት ጠየቀ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ግንቦት 12፣ 2013 ― ድንበር የለሹ የጋዜጠኞች ቡድን በቅርቡ በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለሥልጣን ፍቃዱ የታገደበት የኒውዮርክ ታይምስ እና ብሉምበርግ ዘጋቢ ሳይመን ማርክስ ፍቃድ ተመልሶለት በድጋሚ እንዲሠራ እንዲፈቀድለት ጠይቋል፡፡

ጋዜጠኛው በዘገባዎቹ ምክንያት ለወራት በማስጠንቀቂያ ሲሠራ መቆየቱን ያስታወሰው የድንበር የለሽ የጋዜጠኞች ቡድን፣ ትግራይ ክልል በማቅናት በሠራው ዘገባ እና ከሱዳን ጋር ባለው የድንበር ውጥረት ላይ ያሰናዳው ሌላኛው ዘገባው ለእግዱ ሰበብ መሆኑን ጠቅሷል፡፡

እንድ ቡድኑ የአየርላንድ ዜግነት ያለው ሳይመን ማርክስ የዘጋቢነት ፍቃዱ ከታገደበት በኋላ ላለፉት በርካታ ሳምንታት እንዲመለስለት የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣንን ቢወተውትም፣ ከጥቅምት ወር በፊት ፍቃዱ እንደማይመለስለት ተነግሮታል፡፡

ይህ በመሆኑም ጋዜጠኛው ቀጣዩን ምርጫ እንዳይዘግብ እንደሚያደርገው በመግለጽ፣ የጋዜጠኞች ቡድኑ በጉዳዩ ላይ የባለሥልጣኑን ዳይሬክተር አቶ መሐመድ ኢድሪስን ብጠይቅም ምላሽ አላገኘሁም ብሏል፡፡

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለሥልጣን የጋዜጠኛውን ፍቃድ ያገዱት ‹‹ሚዛናዊ ያልሆነ ዘገባ›› በማቅረቡ መሆኑን አሳውቆ ነበር፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img