Tuesday, October 8, 2024
spot_img

ብሊንክን እና ሐቪስቶ በትግራይ ክልል ያላቸውን ስጋት ገለጹ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ግንቦት 12፣ 2013 ― የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ኃላፊ አንቶንዮ ብሊንክን እና ባለፉት ወራት ሁለት ጊዜ በኢትዮጵያ ጉብኝት ያደረጉት የአውሮፓ ኅብረት ልዩ መልእክተኛ እና የፊንላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፔካ ሐቪስቶ በትላንትናው ዕለት በአይስላንድ ዋና ከተማ ሬይኪያቪክ በተገናኙበት ወቅት በትግራይ ባለው ሁኔታ ስጋታቸውን ገልጸዋል፡፡

ሁለቱ መሪዎች የትግራይን ስጋት የገለጹት በአጠቃላይ በአፍሪካ ቀንድ ያለውን ሁኔታ ሁኔታ ላይ ባነሱበት ወቅት ነው፡፡

ከወራት በፊት ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ትግራይ ክልልን የጎበኙት የአውሮፓ ኅብረት ልዩ ልዑክ ፔካ ሐቪስቶ መንግሥት ቀድሞ በገለጸው መሠረት የኤርትራ ወታደሮች የኢትዮጵያን መሬት ለመውጣታቸው ማረጋገጫ እንዳላገኙ መናገራቸው የሚታወስ ነው፡፡

በተመሳሳይ የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ኃላፊ አንቶኒ ብሊንክን ከሰሞኑ በትግራይ ክልል ሰብዓዊ ርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ተረጂዎች ርዳታ የሚያቀርቡ የተራድኦ ድርጅቶችን ወታደራዊ ኃይሎች እያስተጓጎሉ እንደሚገኙ ገልጸው ነበር፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img