Tuesday, October 8, 2024
spot_img

የአሜሪካ ሴኔት የባይደን አስተዳደር የኤርትራ ጦር ከትግራይ እንዲወጣ በማንኛውም መንገድ ግፊት እንዲያደርግ የሚጠይቅ የውሳኔ ሐሳብ አጸደቀ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ግንቦት 12፣ 2013 ― የአሜሪካ ሴኔት ባደረገው ስብሰባ የባይደን አስተዳደር የኤርትራ ጦር ከትግራይ እንዲወጣ፣ በትግራይ ሁሉም የጦርነቱ ተሳታፊ አካላት የተኩስ አቁም እንዲያደርጉ፣ ያልተገደበ የሰብአዊ አቅርቦት እንዲኖር እንዲሁም የተፈጸሙ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት በገለልተኛ አካል እንዲጣራ የሚጠይቀውን ውሳኔ ማለትም ሪዞዞሽን 97 በሙሉ ድመጽ ማጽደቁ ተሰምቷል፡፡

የአሜሪካ ሴኔት በተመሳሳይ ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ የውሳኔ ሐሳቦችን ማሳለፉ አይዘነጋም፡፡ የባይደን አስተዳደር የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ኃላፊ የሆኑት አንቶንዮ ብሊንክንም በተደጋጋሚ ባወጧቸው መግለጫዎች የኤርትራን ወታደሮች እና የተኩስ አቁምን በተመለከተ ተመሳሳይ አቋም ሲያንጸባርቁ መቆየታቸው የሚታወቅ ነው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img