ከዚህ በላይ የተያያዘው በመጪው አገራዊ ምርጫ የተመዝጋቢ መራጮችና የሕዝብ ቁጥር ንጽጽራዊ አኃዝ የሚያመለክት መረጃ ነው፡፡
ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ግንቦት 7፣ 2013 ይፋ ባደረገው መረጃ መሠረት ለምርጫው 36,245,444 ሰዎች ለምርጫው ተመዝግበዋል፡፡
ሆኖም በአገሪቱ የተለያዩ ክልሎች የተመዘገበው የመራጭ ቁጥር ዕድሜያቸው ለመራጭነት ከደረሱ ሰዎች ጋር ተቀራራቢነት አለው በሚል ትችት ተሰንዝሮበታል፡፡
ትችቹ ከተሰነዘረባቸው ክልሎች መካከል አንደኛው ከሆነው ከሶማሊ ውጭ ከሌሎች ክልሎች እስካሁን ድረስ የተሰጠ ምላሽ አልተሰማም፡፡
የሶማሊ ክልል ርእሰ መስተዳደር አቶ ሙስጠፌ መሐመድ በሰጡት ማብራሪያ በሶማሊ ክልል አጠቃላይ አለ ከሚባለው 6 ነጥብ 7 ሚሊዮን ሕዝብ መካከል 3 ነጥብ 9 ሚሊዮን መራጮች መመዝገባቸው ከፍተኛ የሚባል ቢሆንም፣ ልዩነቱን ያመጣው ባለፉት ሦስት ዓመታት በክልሉ የተፈጠረው ትክክለኛ ያልሆነ የሕዝብ አሰፋፈር መሆኑን አመልክተዋል፡፡
በዚህም ከሌሎች ክልሎች ወደ ክልሉ የመጡ 600 ሺሕ ሰዎች መኖራቸውን ያመለከቱ ሲሆን፣ በተጨማሪም ከኬንያ የስደተኞች መጠለያ፣ ከሶማሊላንድ፣ ከፑንትላንድ እና ከደቡብ ሶማሊያ የተመለሱ 700 ሺሕ ሰዎችም እንዳሉ ጠቅሰዋል፡፡
በምርጫው ተመዝግበዋል የተባሉ የሁሉንም ክልሎች ዕድሜያቸው ለመራጭነት የደረሱ እና ለመራጭነት የተመዘገቡ መራጮች ንጽጽር ሙሉውን ያግኙ፡፡