Wednesday, November 27, 2024
spot_img

በእስራኤል እና ሐማስ ግጭት ሰበብ በጋዛ በአንድ ሰዓት ውስጥ በአማካኝ 3 ልጆች ጉዳት ይደርስባቸዋል ተባለ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ግንቦት 9፣ 2013 ― የእስራኤል እና ሀማስ ግጭት ከተከሰተ ዛሬ ወደ ሁለተኛ ሳምንት ተሸጋግሯል፡፡ ግጭቱን ተከትሎም ሀማስ ከ3 ሺሕ በላይ ሮኬቶችን ወደ እሰራኤል የተለያዩ ከተሞች ያስወነጨፈ ሲሆን፣ እስራኤል በአጸፋው በተከታታይ በጋዛ ሰርጥ የአየር ድብደባዎችን እያካሄደች ነው።

ሕፃናትን ሰለባ በማድረግ ላይ ነው በተባለው ይህ የእስራኤል እና ሀማስ ግጭት፣ በጋዛ ብቻ በአንድ ሰዓት ውስጥ በአማካኝ ሦስት ሕፃናት ላይ ጉዳት እየደረሰ መሆኑን ነው ዓለም አቀፉ የሕፃናት አድን ድርጅት አስታውቋል፡፡

ግጭቱን ተከትሎም የ60 ሕፃናት ሕይወት ያለፈ ሲሆን፣ ከእነዚህም ውስጥ 58 ከፍልስጤም፣ 2 ደግሞ ከእስራኤል መሆኑ ተነግሯል።

በጋዛ ከ1 ሺህ በላይ ሰዎች በግጭቱ አካላዊ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ 366ቱ ህጻናት መሆናቸውን ነው የህጻናት አድን ድርጅት ያስታወቀው።

የእስራኤል እና የሀማስን ግጭት ተከትሎ እስራኤል በጋዛ ሰርጥ እያካሄደች ያለው የአየረ ድብደዳ ዛሬ ስምንተኛ ቀኑን ይዟል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img