አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ግንቦት 9፣ 2013 ― ከትላንት ግንቦት 8፣ 2013 ምሽት ጀምሮ በኢትዮጵያ ሁሉም ቦታዎች ፌስቡክ፣ ኢንስታግራም እና ዋትስ አፕ የተሰኙት የማኅበራዊ ትስስር መገልገያዎች መቋረጣቸው መነገሩ የሚታወስ ነው፡፡
በጉዳዩ ላይ አል ዓይን ኢትዮ ቴሌኮምን ጠይቄ አገልግሎቱ ከኩባንያው እውቅና ውጭ መቋረጡን ሰምቻለሁ ብሎ ዘግቧል፡፡
ከትላንት ምሽት አንስቶ የተቋረጡት የተጠቀሱት የማኅበራዊ ትስስር ድረ ገጾች ዛሬ ረፋድ ላይ በድጋሚ አገልግሎት መጀመራቸው ታውቋል፡፡