አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ግንቦት 9፣ 2013 ― የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ እርዳታ ማስተባበሪያ ቢሮ ባወጣው ወቅታዊው የትግራይ ክልል ሁኔታ ላይ የረድኤት ድርጅቶች የአድዋን ደቡባዊ አካባቢዎች መድረስ አልቻሉም ብሏል፡፡
ቢሮው የረድኤት ድርጅቶች ሊደርሱባቸው አልቻሏቸውም ያለው የአቢ አዲን አካባቢ ሲሆን፣ በዚህ አካባቢ እና አጎራባች አካባቢዎች ግጭት እንደሚስተዋልና ከአቢ አዲ ሀገረ ሰላም በሚወስደው መንገድ ላይ ያለው ሁኔታም ተለዋወጭ መሆኑን አመልክቷል፡፡
በተጨማሪም በክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች ግጭቶች እንደሚስተዋል የገለጸው ቢሮው፣ በትግራይ ምሥራቂቃዊ ዞን በሐውዜን ከተማ እና ዙሪያውን ውጥረት እንደሚስተዋል ነው የጠቆመው፡፡
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ እርዳታ ማስተባበሪያ ቢሮ በትግራይ ክልል ባለፉት ስድስት ወራት በአጠቃላይ ሰባት የተራድኦ ሠራተኞች እንደተገደሉ በሪፖርሩ ጨምሮ አሳውቋል፡፡