Monday, September 23, 2024
spot_img

የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ሦስት የቻይና ዜጎችን ማገቱን አስታወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ግንቦት 9፣ 2013 ― ኩምሳ ድሪባ ወይም ጃል መሮ ይመራዋል የሚባለው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (መንግሥት እንደሚጠራው ሸኔ) ሦስት የቻይና ዜጎችን ማገቱን አስታውቋል፡፡

ሦስቱን ቻይናዊያን ማገቱን ያስታወቀው ቡድኑ፣ በምሥራቅ ወለጋ መንዲ አካባቢ እንደታገቱና በማእድን ማውጣት ሥራ ላይ እንደነበሩ ነው ያመለከተው፡፡

የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ቃል አቀባይ ነው በሚባለው ኦዳ ተርቢ ትዊተር ላይ እንደሠፈረው ከሆነ ሁዋንግ፣ ሂ እና ዋንግ የተባሉት ቻይናዊያን በአሁኑ ወቅት በጥሩ ጤንነት እና በመልካም ሁኔታ ተይዘዋል፡፡

ጉዳዩን አስመልክቶ በመንግሥት በኩል እስካሁን የተሰጠ መግለጫ የለም፡፡

በመንግሥት ሸኔ ተብሎ የሚጠራው ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት የሚለው ቡድን ከቀናት በፊት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከሕወሃት ጋር በአንድነት በአሸባሪነት መፈረጁ የሚታወስ ነው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img