Tuesday, October 8, 2024
spot_img

ምርጫ ቦርድ እስከ ሳምንቱ አጋማሽ ድረስ ከ36 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ለመራጭነት መመዝገባቸውን አስታወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ግንቦት 7፣ 2013 ― የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እስከ ሳምንቱ አጋማሽ ረቡዕ ግንቦት 4፣ 2013 ድረስ ባደረግኩት ቆጠራ ከ36 ሚሊዮን በላይ ሰዎ ለመራጭነት የድምጽ መስጫ ካርድ ወስደዋል ብሏል፡፡

ይህንኑ የቦርዱ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ በዛሬው እለት ቦርዱ በመራጮች ምዝገባ ሂደት እና ባጋጠሙ ችግሮች ዙሪያ ከፓለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ጋር በተወያየበት ወቅት ገልጸዋል፡፡

በዚህም ለምርጫው ይመዘገባል ተብሎ ተገምቶ ከነበረው መራጭ መካከል 78 ነጥብ 3 በመቶ ያህሉ መመዝገቡ ነው የተገለጸው፡፡

ምርጫ ቦርድ ከመጋቢት 16፣ 2013 ጀምሮ ሲያካሄደው የቆየውና ለሦስት ጊዜያት ያህል ያራዘመው በመላው አገሪቱ በ11 ክልሎች እና የከተማ መስተዳድሮች ሲካሄድ የቆየው የመራጮች ምዝገባ በትላንትናው እለት ተጠናቋል፡፡

በአገሪቱ ለስድስተኛ ጊዜ የሚካሄደው አገራዊ ምርጫ በተያዘው ግንቦት 28 እንደከሚካሄድ ቀጠሮ የተያዘለት ሲሆን፣ በአዲስ አበባ እና በድሬዳዋ ከተማ መስተዳድሮች ደግሞ ከሳምንት በኋላ ሰኔ 5 ይካሄዳል ተብሏል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img