Tuesday, October 8, 2024
spot_img

የአውሮፓ ኅብረት በትግራይ ገጠራማ ቦታዎች ላይ እርዳታ እንዳይደርስ ወታደሮች እየከለከሉ መሆኑን አስታወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ግንቦት 7፣ 2013 ― የአውሮፓ ኅብረት ይህን ያለው በውጭ ጉዳዮች ከፍተኛ ተወካይ ጆሲፕ ቦሬል እና በቀውሶች አያያዝ ኮሚሽነር ያኒዝ ሌናርቺች በኩል በትግራይ ክልል ስላለው የረድዔት ተደራሽነት ጉዳይ ባወጣው መግለጫው ነው፡፡

በትግራይ ክልል የሰብዓዊ ረድኤት ተደራሽነትን ወታደራዊ ኃይሎች እያያደናቀፉ መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አረጋግጧል ያሉት ጆሲፕ ቦሬል እና ያኒዝ ሌናርቺች፣ የአውሮፓ ኅብረት ለሁሉም አካባቢዎች የረድዔት ተደራሽነት እንዲረጋገጥ እንዲሁም የኤርትራ ወታደሮች በአስቸኳይ ከአካባቢው እንዲወጡ በተደጋጋሚ ሲጠይቅ መቆየቱንም አስታውሰዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት በበኩላቸው እነዚህን ሁለቱንም ጥያቄዎች ተፈፃሚ ለማድረግ ቃል የገቡ ቢሆንም፣ መሬት ላይ የሚታየው እውነታ ግን ሰብዓዊ ቀውሱ ከሁሉም በላይ የከፋ በሆነባቸው ገጠራማ አካባቢዎች እርዳታ እንዳደርስ ወታደራዊ ኃይሎች እየከለከሉ መሆኑን ነው ብለዋል።

የአውሮፓ ኅብረት ባለሥልጣናቱ በመግለጫቸው ሰብዓዊ ረድዔትን በጦርነት መሳሪያነት መጠቀም ከባድ የዓለም አቀፍ ሰብዓዊ ረድዔት ሕግጋትን የሚጥስ ነው ያሉ ሲሆን፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎችን ሕይወት አደጋ ላይ የሚጥል መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

አክለውም ዜጎች ለበረታ ረሃብ እንዳይዳረጉ መከላከል እንዲቻል በአስቸኳይ የተሟላ እርዳታ መድረስ አለበት ያሉት ተወካዮቹ፣ እርዳታ በአፋጣኝ እንዳይደርስ ሆን ብለው የሚያደናቅፉም ሊጠየቁ ይገባል ብለዋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img