Tuesday, October 8, 2024
spot_img

አሜሪካ በትግራይ ጦርነት የተኩስ አቁም እንዲደረግ እንደምትሠራ አሳወቀች

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ግንቦት 5፣ 2013 ― አሜሪካ በትግራይ ባለው ጦርነት የተኩስ አቁም እንዲደረግ ከዓለም አቀፍ አጋሮች ጋር እንደምትሠራ በዛሬው እለት ሰሞነኛውን የጄፍሪ ፌልትማንን የምሥራቅ አፍሪካ ጉብኝት አስመልክቶ በውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቷ ቃል አቀባይ ጽሕፈት ቤት በኩል ባወጣችው መግለጫ አስታውቃለች።

አገሪቱ ጦርነቱ አብቅቶ አስቸኳይ ድጋፍ ለሚስፈልጋቸው ድጋፍ እንዲደረግና በሰብአዊ መብት ጥሰት ላይ የተሳተፉ ተጠያቂ እንዲሆኑ እንደምትሠራም በመግለጫው ተጠቅሷል።

በትግራይ ያጋጠመው ችግር ተስፋ ተጥሎበት የነበረው ሃገራዊ ለውጥ ለገጠሙት ዘርፈ ብዙ ችግሮች ማሳያ ሆኖ በምልክትነት ሊጠቀስ እንደሚችልም ነው መግለጫው ያመለከተው።

በሌላ በኩል አገሪቱ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የተቋረጠው የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የሦስትዮሽ የድርድር ሂደት በአስቸኳይ እንዲጀመር አሳስባለች፡፡

በመግለጫዋ የአፍሪካ ቀንድ በወሳኝ የለውጥ ምዕራፍ ላይ እንደሚገኝ የጠቆመችው አሜሪካ፣ በቀጣይ ሳምንታትና ወራት የሚተላለፉ ውሳኔዎች ለቀጠናው ህዝቦች ለራሷ ፍላጎቶች ጭምር ትልቅ እንደምታ እንደሚኖራቸው አስታውቃለች፡፡

የቀጠናው ቀውሶች ለመፍታት እንዲሁም ዜጎች ድመጻቸውን የሚያሰሙባትና መንግሥታት ተጠያቂ የሚሆኑባት የበለፀገችና የተረጋጋች አፍሪካን እውን ለማድረግ አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኗንም ነው የገለጸችው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img