Monday, October 7, 2024
spot_img

ምርጫ ቦርድ የድምጽ መስጫ ወረቀት ኅትመት ጋር በተገናኘ ያለውን ሂደት የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችን ወደ ውጭ በመላክ ማስጎብኘቱን አሳወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ግንቦት 5፣ 2013 ― የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከፓለቲካ ፓርቲዎች እና ሚዲያዎች የተወጣጣ የልኡካን ቡድን ወደ ደቡብ አፍሪካ በመላክ የድምጽ መስጫ ወረቀት ኅትመቱን እንዲጎበኙ ማድረጉን አስውቋል፡፡

በቦርዱ ከፍተኛ አመራር ፍቅሬ ገብረሕይወት ለተመሩት ከፓርቲዎች እና ከሚዲያዎች ለተውጣጡ ተወካዮች የኅትመት ሥራውን ከሚያካሂዱት ሁለት የኅትመት ድርጅቶች አንዱ በሆነውና በደቡብ አፍሪካ የሚገኘውን የሬን ፎርም ኅትመት ማኅበር ያለውን ሒደት ማሳየቱን ነው የገለጸው፡፡

እንደ ምርጫ ቦርድ በደቡብ አፍሪካ የሚካሄደው ኅትመት የድምጽ መስጫ ወረቀት ኅትመቱን 45 በመቶ የሚሸፍን ሲሆን፣ ይህውም የደቡብ ሕዝቦች፣ የአማራ፣ የሲዳማ ክልልና የደቡብ ምዕራብ ሕዝቦች ሕዝበ ውሣኔን ያካትታል፡፡

ቀሪውና 55 በመቶ የሚሸፍነው የኅትመት ሥራ ዱባይ በሚገኘው አል-ጉህራር ማኅበር እየተከናወነ እንደሚገኝ የተገለጸ ሲሆን፣ ለአራት ቀናት በቆየው ጉብኝትም የብልጽግና ፓርቲ፣ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)፣ የህብር ኢትዮጵያ ተወካይ (ህብር)፣ የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ኢሶዴፓ) እንዲሁም የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ከፍተኛ አመራሮች፣ የፓለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢው እና የሚዲያ አካላት መሳተፋቸውን የቦርዱ መረጃ ያመለክታል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img