Sunday, November 24, 2024
spot_img

ባልደራስ አገር አቀፍ ምርጫው ፍትሐዊነት የሚጎድለው እና በችግሮች የተተበተበ ነው አለ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ግንቦት 5፣ 2013 ― በተያዘው ወር መጨረሻ የሚካሄደው አገር አቀፍ ምርጫ ከቅድም ምርጫ የመራጮች ምዝገባ ሂደት አንጻር ሲፈተሽ ነጻ መሆንና ፍትሐዊነት የሚጎድለው፣ መርሆዎችን ያልተከተለ እና በበርካታ ችግሮች የተተበተበ ነው ሲል ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ነቅፏ።

ፓርቲው በምርጫው ሒደት ታይተዋል ላላቸው ችግሮች ዋነኛው ተጠያቂው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ነው ብሏል።

ባልደራስ ይህን ያለው በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች የታዩ ተግዳሮቶችን የሚዳስስ ባለ 12 ገጽ የዳሰሳ ጥናት በዛሬው እለት ይፋ ባደረገበት ወቅት ነው። ዳሰሳው የሸፈነው 218 የምርጫ ጣቢያዎችን እንደሆነ ፓርቲው በራስ አምባ ሆቴል በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።
በምርጫ ጣቢያዎችን እና በመራጮች ምዝገባ ሂደት የታዩ ችግሮችን ነቅሶ ለማውጣት እንደተደረገ የተገለጸውን ይህ የዳሰሳ ጥናት ያከናወነው ፓርቲው ለዚሁ ጉዳይ ያቋቋመው ቡድን ነው ተብሏል። በጥናቱ ከተደረሰባቸው ግኝቶች መካከል ከብሔር እና የእምነት ማንነት ጋር በተያያዘ የምርጫ ካርድ ማደል አንዱ መሆኑ ፓርቲው ገልጿል።

‹‹የምርጫ ካርድ መውሰድ የማይገባቸው፤ ምናልባትም ከሌላ አካባቢ የመጡ ዜጎች የሐሰት ምስክር በማቅረብ የምርጫ ካርድ እንደሚወስዱ በጥናቱ የተረጋገጠ ጉዳይ ነው›› ሲል ባልደራስ በዳሰሳ ጥናቱ አመልክቷል።

‹‹አንዳንድ ሰዎች በርካታ የምርጫ ካርዶች ያለግባብ ማውጣታቸው፤ ከአጎራባች የኦሮሚያ ወረዳዎች እየመጡ ሰዎች ካርድ መውሰዳቸው፣ የምርጫ ቦርድ ከነዋሪዎች ጋር ተመጣጣኝነት ያለው የምርጫ ጣቢያዎች አለመክፈቱ የችግሮቹ መንስኤዎች እንደሆኑ ለመረዳት ይቻላል›› ማለቱንም የዘገበው ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ድረ ገጽ ነው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img