Monday, October 7, 2024
spot_img

በደምቢ ዶሎ አንድ ወጣት በመንግሥት ታጣቂዎች በአደባባይ ተረሸነ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ግንቦት 4፣ 2013 ― በኦሮሚያ ክልል ደምቢ ዶሎ ከተማ አማኑኤል ወንድሙ የተባለ በ20ዎቹ መጀመርያ እድሜ ላይ የሚገኝ ወጣት በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ሕዝብ በተሰበሰበበት በአደባባይ በጥይት ተደብድቦ እንደተገደለ የዓይን እማኞች ገለጹ።

የጸጥታ ኃይሎቹ ወጣቱን በጥይት ተኩሰው ከገደሉት በኋላ በደረቱ አካባቢ ሽጉጥ አንጠልጥለው መሄዳቸውን ከሥፍራው የወጣው የቪዲዮ መረጃ ያመለክታል፡፡

የደምቢ ዶሎ ኮሚዩኒኬሽን ጽ/ቤት በፌስቡክ ገጹ «ሰዎችን ሲገድል በነበረው እና የ ‘አባ ቶርቤ’ ቡድን አባል በሆነው ግለሰብ ላይ እርምጃ ተወሰደ» በሚል በፎቶ የታጀበ መልእክት አስተላልፏል። የከተማው ጽ/ቤት በፌስቡክ ገጹ ላይም ወጣቱ ከመገደሉ በፊት የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል አሠራጭቷል።

ቢቢሲ የቄለም ወለጋ ዞን የደኅንነት ቢሮ ኃላፊ አቶ ተሰማ ዋሪዮ በጉዳዩ ላይ አነጋግሬ ወጣቱ ቆስሎ ከተያዘ በኋላ ለሕዝብ እንዲታይ ተደረገ እንጂ በአደባባይ አልተገደለም ብለውኛል ሲል ዘግቧል፡፡ «ወንጀለኛ መሆኑ ተረጋግጧል» የሚሉት አቶ ተሰማ፤ ይህ ወጣት ሁለት ሰዎች በጥይት መትቶ እያመለጠ ሳለ በፀጥታ ኃይሎች በጥይት ተመትቶ መያዙን ነው የሚናገሩት።


ወጣቱ ለፍርድ ሳይቀርብ ለምን መሰል እርምጃ ተወሰደበት በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ ኃላፊው «ወንጀለኛ መሆኑ ተረጋግጧል» ከማለት ውጪ ተጨማሪ ማብራሪያ አልሰጡም።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img