Sunday, November 24, 2024
spot_img

በሰሜን ምዕራብ ትግራይ የኤርትራ ወታደሮች መንገዶችን ከዘጉ አንድ ወር ማስቆጠሩ ተነገረ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ግንቦት 4፣ 2013 ― በቅርቡ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከትግራይ ክልል ይወጣሉ ቢባልም እስካሁን እንደሚገኙ የሚነገርላቸው የጎረቤት አገር ኤርትራ ወታደሮች በሰሜን ምእራብ ትግራይ መንገዶን ከዘጉ አንድ ሊቆጠር መሆኑን ሲኤንኤን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የፀጥታ ኃላፊዎች ነግረኛል ብሎ ዘግቧል፡፡

እንደ ኃላፊዎቹ ከሆነ የኢትዮጵያ መንግሥት በክልሉ የሚገኙ የኤርትራ ወታደሮችን ማዘዝ አይችልም፡፡ እነዚሁ ወታደሮቹ በማእከላዊ ትግራይ በተመሳሳይ መንገዶችን ከዘጉ ሁለት ሳምንት ማስቆጠሩም ተነግሯል፡፡

በአንዳንድ ሥፍራዎች ላይ የቀድሞውን የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት መለያ ለብሰው እንደሚታዩ የተነገረላቸው እነዚህ የኤርትራ ወታደሮች፣ በክልሉ ፈጽመውታል ከሚባለው የጅምላ ግድያ፣ አስገድዶ መድፈር በተጨማሪ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦትን እያሰናከሉ እንደሚገኙም ነው በዘገባው የተመላከተው፡፡

በትግራይ በጥቅምት የመጨረሻ ቀናት የተነሳውን የፌዴራል መንግሥት እና የሕወሃት ኃይሎች ጦርነት ተከትሎ ወደ ክልሉ የዘለቁት የኤርትራ ወታደሮች ይወጣሉ ከተባለ በርካታ ሳምንታት ተቆጥረዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img