Sunday, October 6, 2024
spot_img

ኢትዮ ቴሌኮም ‹‹ቴሌ ብር››ን በይፋ አስጀመረ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ግንቦት 4፣ 2013 ― ኢትዮ ቴሌኮም ‹‹ቴሌ ብር›› የተሰኘውን የሞባይል የክፍያ ሥርዐት ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ትላንት ምሽት በይፋ አስጀምሯል፡፡

የኢትዮ ቴሌኮም ‹‹ቴሌ ብር›› የሞባይል የክፍያ ሥርዓትን ያስጀመሩት የዕለቱ የክብር እንግዳ የነበሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ናቸው፡፡

የሞባይል ኔትወርክ ባለባቸው አካባቢዎች ሁሉ በየትኛውም የስልክ ቀፎ ዐይነት መጠቀም ያስችላል የተባለው የቴሌ ብር የክፍያ ሥርዐት፣ የአየር ሰዓት ለመሙላት እና ሌሎች አገልግሎቶች ክፍያዎችን ለመፈጸም እንደሚያስችል ተነግሮለታል።

ቴሌ ብር በኪስ እንደሚያዝ ገንዘብ ቦርሳ በሀገር ውስጥ እንዲሁም በዓለም አቀፍ ደረጃ ገንዘብን ለመያዝ፣ ለመላክና ለመቀበል እንዲሁም ክፍያን በሞባይል ለመፈጸም እንደሚያስችል የተገለጸ ሲሆን፣ ከዚያም ባለፈ ከሀገር ውጪ ካለው ዳያስፖራ ገንዘብ ለመቀበል፣ ገንዘብ ለመቆጠብ፣ ብድር ለማግኘት እና የባንክ አካውንት ከቴሌብር ጋራ እንዲተሳሰር የሚፈቅድ መሆኑ ተመላክቷል።

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወይዘሪት ፍሬሕይወት ታምሩ በሥነ ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ ኩባንያው ባለፉት 127 ዓመታት ካቀረባቸው አገልግሎቶች ለየት ያለ ነው ያሉተን የቴሌ ብር አገልግሎት በማቅረቡ እንኳን ደው ያላች ብለዋል፡፡

ቴሌ ብር በገጠር የሀገሪቱ ክፍል እና በዝቅተኛ የኢኮኖሚ ደረጃ ለሚገኙ የማኅበረሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው ያሉት ፍሬሕይወት፣ በኢትዮጵያ የተጀመረውን የዲጂታል ኢኮኖሚ ለመደገፍ እና ዘመናዊ የኢኮኖሚ ሥርዓን ለመዘርጋት አጋዥ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

ይህ መተግበሪያ በአምስት ቋንቋዎች እንደሚገኝም ሥራ አስፈጻሚዋ ፍሬሕይወት ታምሩ ገልጸዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img