Sunday, September 22, 2024
spot_img

የአውሮፓ ኅብረት ስድስት የምርጫ ታዛቢዎች ሊልክ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ግንቦት 3፣ 2013 ― ከቀናት በፊት ለመጪው ምርጫ ታዛቢዎችን እንደማይልክ አሳውቆ የነበረው የአውሮፓ ኀብረትን ጨምሮ አራት ዓለም አቀፍ ተቋማት ለመጪው ጠቅላላ ምርጫ ታዛቢዎችን ለመላክ መስማማታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የሚኒስቴሩ ቃል አቃባይ ዲና ሙፍቲ ዛሬ በሰጡት ሳምንታዊ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንዳሉት ምርጫውን በዋናነት ይታዘባል ተብሎ ከሚጠበቀው የአፍሪካ ኅብረት በተጨማሪ ሁለት የአሜሪካ እና አንድ የሩሲያ ተቋማት ታዛቢዎችን ወደ ኢትዮጵያ ይልካሉ።

በአሜሪካ በኩል ምርጫውን ለመታዘብ ፍቃደኝነታቸውን የገለጹት ኢንተርናሽናል ሪፐብሊካን ኢንስቲትዩት እና ናሽናል ዲሞክራቲክ ኢንስቲትዩት የሚባሉ ተቋማት እንደሆኑ አምባሳደር ዲና ተናግረዋል።

የምርጫ መታዘብ ዕቅዱን መሰረዙን ባለፈው ሳምንት ያስታወቀው የአውሮፓ ኅብረት፣ ስድስት አባላት ያሉበትን የባለሙያዎች ቡድን እንደሚልክ ማስታወቁንም አክለዋል።

የአውሮፓ ኅብረት የባለሙያዎች ቡድን ለመላክ የተስማማው በኢትዮጵያ በኩል የአቋም ለውጥ ተደርጎ ነው ወይ ተብለው የተጠየቁት ዲና፣ ‹‹ኢትዮጵያ አሁንም አቋም አልቀየረችም›› ያሉ ሲሆን፣ የሚመጡትን ባለሙያዎች በዚያው አቋም መሆኑን ገልጸዋል፡፡

አክለውም ኮሚሽኑ ማስገባት አለብኝ ያለውን ‹‹ቪሳት›› የተሰኘ መሳሪያ አንዲሁም ከምርጫ ኮሚሽን አስቀድሞ መግለጫ ልስጥ ማለቱንም እንዳልተፈቀድለት ተናግረዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img