Friday, November 22, 2024
spot_img

በአክሱም በመድፈር ወንጀል የተጠረጠሩ የመከላከያ አባላት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አቃቤ ሕግ አስታወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ግንቦት 3፣ 2013 ― በአክሱም በመድፈር ወንጀል የተጠረጠሩ የመከላከያ አባላት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን በአክሱም ከተማ ስለተፈፀሙ ግድያዎች እና መደፈሮች መግለጫ የሰጠው የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ አሳውቋል፡፡

ከክልሉ ፖሊስ በተገኘው መረጃ መሠረት የመድፈር ጥቃት ደርሶብናል ብለው ሪፖርት ያደረጉ ሴቶች ቁጥር 116 መሆኑን የተናገሩት ምክትል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ፍቃዱ ጸጋ፣ በወንጀል ድርጊቱ ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር የዋሉ የአገር መከላከያ ሠራዊት እና የፌደራል ፖሊስ አባላት መኖራቸውን ገልጸዋል፡፡

አቶ ፍቃዱ የአገር መከላከያ ሠራዊት አባላት ድርጊቱን ፈጽመውታል የተባለው በግዳጅ ላይ እያሉ ስለሆነ ጉዳያቸው በጦር ፍርድ ቤት ይታያል ያሉ ሲሆን፣ የፌደራል ፖሊስ አባላትን በተመለከተ የክልሉ ፖሊስ ምርመራ አጠናቆ ለክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ወይም ደግሞ ለፍትሕ ቢሮ መዝገቡ ተላልፎ ተሰጥቷል ሲሉ አስረድተዋል።

እንደ ምክትል ጠቅላይ አቃቤ ሕጉ ገለጻ የፍትሕ ቢሮ ጉዳዩን መርምሮ ውሳኔ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።

ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ከሌሎች የፍትሕ አካላት ጋር በመተባበር የትኛውንም ወንጀል ፈጻሚ ሙያዊ ደረጃውን በጠበቀ መርምሮ ጥፋተኞችን ለሕግ ለማቅረብ ዝግጁነት አለው ብለዋል።

በትግራይ ክልል ጥቅምት 24፣ 2013 በፌደራል መንግሥቱ እና በሕወሓት ኃይሎች መካከል ግጭት ከተቀሰቀሱ ወዲህ በርካታ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መድረሳቸውን የተለያዩ ዓለም አቀፍ ሰብዓዊ መብት ድርጅቶች እና ኢሰመኮ ማስታወቃቸው አይዘነጋም፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img