Sunday, September 22, 2024
spot_img

አምባሳደር ጄፍሪ ፌልትማን ወደ ኢትዮጵያ መጥተዋል

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ግንቦት 2፣ 2013 ― ከባለፈው ሳምንት አንስቶ በግብጽ፣ ኤርትራ እና ሱዳን ጉብኝት ላይ የነበሩት የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ጄፍሪ ፌልትማን ወደ ኢትዮጵያ መጥተዋል፡፡

በዛሬው እለት ከውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ስለሺ በቀለ ጋር ጋር መወያየታቸው የተነገረው ፌልትማን፣ በቀጣይ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር ይወያያሉ ተብሎ ተጠብቋል፡፡

በዛሬው እለት ዲፕሎማቱ እና ዶክተር ስለሺ ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ እየገነባች ባለው ታላቁ የሕዳሴ ግድብ እና የሦስትዮሽ ድርድር ላይ አተኩረው መወያየታቸው የተነገረ ሲሆን፣ በዚህ ውይይት ላይ በኢትዮጵያ በኩል የሕዳሴ ግድብ ተደራዳሪዎች ተገኝተዋል ሲል ፋና ዘግቧል፡፡

በጆ ባይደን አስተዳደር በቅርቡ የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ሆነው የተሸሙት አምባሳደር ፌልትማን በቀጣናው ያሉ አለመግባባቶች ፣ በተለይም የሕዳሴው ግድብ ጉዳይ እና የኢትዮጵያና የሱዳን የድንበር ውዝግብ ፣ በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ ለማድረግ በሀገራቸው ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል፡፡

አምባሳደሩ በሱዳን በነበራቸው ቆይታ በሕዳሴው ግድብ ጉዳይ በአፍሪካ ሕብረት መሪነት የተጀመረው ድርድር እንዲቀጥል ማሳሰባቸው ይታወሳል፡፡ ሦስቱም ተደራዳሪ ሀገራት ካልፈቀዱ በስተቀር አሜሪካ ጣልቃ የመግባት ፍላጎት እንደሌላትም ነው የገለጹት፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img