Thursday, November 21, 2024
spot_img

አሜሪካ በኢትዮጵያ የሚስተዋሉ ግጭቶችን ለማስቆም በአስቸኳይ ንግግር እንዲጀመር ጥሪ አቀረበች

አምባ ዲጂታል፤ ቅዳሜ ጥር 25፣ 2016 – የአሜሪካ መንግሥት በኢትዮጵያ የሚስተዋሉ ግጭቶችን ለማስቆም በአስቸኳይ ንግግር እንዲጀመር ጥሪ ያቀረበችው ለስድስት ወራት ተጥሎ የነበረው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መራዘሙን ተከትሎ ነው።

የአገሪቱ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ቢሮ፣ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዋና ኮሚሽነር ከስድስት ወራት በፊት የተደነገገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መራዘሙ አሳሳቢ ነው ማለቱን ተጋርቶታል።

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) ትላንት ረፋድ መንግሥት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የሚያራዝመው ከሆነ በሰብዓዊ መብቶች አያያዝ ላይ ሊያስከትል የሚችለው አሉታዊ ተጽእኖ አሳሳቢ ነው ብለው ነበር።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤቱ ትላንት ዐርብ ጥር 24፣ 2016 በጠራው ልዩ ስብሰባው አባላቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማራዘም በሚቀርብ የውሳኔ ሐሳብ ላይ ውይይት አድርገው ለአራት ወራት አራዝሞታል።

የኢሰመኮ ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) ቀድመው ባሠፈሩት ጽሑፍ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የሚራዘም ከሆነ የግጭት ተጎጂ በሆኑ፣ በሰብዓዊ ቀውስ ውስጥ ባሉ እና ለፍርድ ሳይቀርቡ ለረዥም ጊዜያት በእስር ላይ በሚቆዩ ሰዎች የሰብዓዊ መብት አያያዝ ላይ የሚያመጣው አሉታዊ ተጽእኖ አሳሳቢ ብለው ነበር። ኮሚሽነሩ አክለውም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና መንግሥት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አስፈላጊነት፣ ሕጋዊነት እና ተመጣጣኝነትን በአግባቡ ማጤን እንደሚኖርባቸው በማስታወ፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲደነገግ ላስገደደው ችግር ውይይት ቁልፍ መፍትሄ ነው ሲሉ መክረዋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img