Monday, October 7, 2024
spot_img

የቀድሞ የድምጺ ወያነ ቴሌቪዥን ኃላፊ የመቐለ ኤፍ ኤም ሥራ አስኪያጅ ተደርገው መሾማቸው ተሰማ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ሚያዝያ 29፣ 2013 ― የቀድሞው የትግራይ ቴሌቪዥን እና የድምጺ ወያነ ቴሌቪዥን የአማርኛ ቋንቋ ክፍል ኃላፊ የነበሩት አቶ ዳርእስከዳር መብራህቱ የመቐለ ኤፍ ኤም ሥራ አስኪያጅ ሆነው መሾማቸው ተሰምቷል፡፡ አቶ ዳርእስከዳር ከጣቢያው ሠራተኞች ጋር ይፋዊ የትውውቅ መድረክ ተዘጋጅቶላቸው ሥራቸውን መጀመራቸውን አዲስ ዘይቤ ድረ ገጽ አስነብቧል፡፡

አሁን የመቐለ ኤፍ ኤም ሥራ አስኪያጅ ተደርገው የተሾሙት አቶ ዳርእስከዳር መብራሕቱ ከድምጺ ወያነ ቴሌቪዥን ቀድሞ የኢቲቪ ዶክመንታሪ ክፍል ኃላፊ የነበሩ ናቸው፡፡

በተያያዘ ዜና ከዚህ በፊት እግድ ላይ ከነበሩት የመቐለ ኤፍኤም ጋዜጠኞች መካከል 9 ያህሉ በከባድ ማስጠንቀቂያ ሥራቸውን እንዲቀጥሉ ሲደረግ፣ 4 ጋዜጠኞች የሦስት ቀን ደሞዛቸውን እንዲቀጡ ተወስኗል፡፡

አዲስ ሥራ አስኪያጅ የተሾመለት የመቐለ ኤፍ ኤም በአቶ ሃጋዚ ወልዱ ጊዜያዊ አስተባበሪነት ሲመራ የቆየ ነው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img