Sunday, September 22, 2024
spot_img

የኤርትራው ፕሬዝዳንት የፕሪቶሪያው ስምምነት እንዳይተገበር የፈለገ አገሬን ሰበብ ማድረግ የለበትም ሲሉ ተናገሩ

አምባ ዲጂታል፤ ሐሙስ የካቲት 2፣ 2015 – የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ በፕሪቶሪያው የተፈረመው የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግሥት እና የሕወሓት የሠላም ስምምነት እንዳይተገበር የፈለገ አገራቸውን ሰበብ ማድረግ የለበትም ሲሉ የተናገሩት ዛሬ ሐሙስ በናይሮቢ ከኬንያው አቻቸው ዊሊያም ሩቶ ጋር በነበራቸው ጋዜጣዊ መግለጫ ነው፡፡

አምባ ዲጂታል፤ ሐሙስ የካቲት 2፣ 2015 – የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ በፕሪቶሪያው የተፈረመው የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግሥት እና የሕወሓት የሠላም ስምምነት እንዳይተገበር የፈለገ ኤርትራን ሰበብ ማድረግ የለበትም ሲሉ የተናገሩት ዛሬ ሐሙስ በናይሮቢ ከኬንያው አቻቸው ዊሊያም ሩቶ ጋር በነበራቸው ጋዜጣዊ መግለጫ ነው፡፡

ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ በናይሮቢ ከሩቶ ጋር መግለጫ የሰጡት፤ ትላንት ረቡዕ እና ዛሬን ጨምሮ በአገሪቱ ካደረጉት ይፋዊ የሥራ ጉብኝት በኋላ ነው፡፡

በዚሁ መግለጫ ላይ ኢሳይያስ ከምዕራባዊያን መገናኛ ብዙኃን መገናኛ አባላት የኢትዮጵያን የሠላም ስምምነት በተመለከተ በተከታታይ ጥያቄዎች ተሰንዝሮላቸዋል፡፡ በጋዜጠኞቹ ከተሰነዘሩት ጥያቄዎች መካከል ስለ ስምምነቱ ትግበራ፣ በጦርነቱ የሞቱ የኤርትራ ወታደሮች ብዛት እና በኢትዮጵያ ይገኛሉ ስለሚባሉ ወታደሮቻቸው ጉዳይ ይገኝበታል፡፡

ጋዜጠኞቹ በተከታታይ ተመሳሳይ ጥያቄዎችን ያከታተሉባቸው ኢሳይያስ፤ ጥያቄዎቹን በቀጥታ ከመመለስ ይልቅ ጋዜጠኞቹን እና ጥያቄያቸውን አጣጥለዋል፡፡ የሠላም ስምምነቱን በተመለከተ ጉዳዩ የኢትዮጵያ መሆኑን የጠቀሱት ፕሬዝዳንቱ እንዳይተገበር የሚፈልግ ኤርትራን ሰበብ ማድረግ የለበትም ያሉትም በዚሁ ወቅት ነው፡፡

በዚሁ መግለጫ ወቅት በኤርትራ እና ኢትዮጵያ መካከል ቅራኔ ለመፍጠር የሚፈልጉ አካላትን ይብቃችሁ ሲሉ የተደመጡት ኢሳይያስ፤ ኢትዮጵያ አነ ኢትዮጵያውያውያን የሠላም አየሩን ያጣጥሙበት ብለዋል፡፡  ከፕሪቶሪያም ሆነ ከናይሮቢው ስምምነት ጋር በተገናኘ ኤርትራ በጉዳዩ ላይ ያለ ኢትዮጵያ ፍቃድ የመግባት ፍላጎት እንደሌላትም ተናግረዋል፡፡

በኢሳይያስ አፈወርቂ የሚታዘዘው የኤርትራ ጦር፤ ሁለት ዓመት ተካሄዶ ባለፈው ጥቅምት በሠላም ስምምነት በተቋጨው የፌዴራል መንግስት እና ሕወሓት ጦር ጦርነት ከመንግስት ጎን ተሰልፎ መዋጋቱ ይታወሳል፡፡ የኤርትራ ባለሥልጣናት ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ጦሩ በኢትዮጵያ መሬት ላይ መኖሩን ሲያስተባብሉ ቆይተዋል፡፡

በመንግሥት እና ሕወሓት የሠላም ስምምነት የኤርትራ ጦር ከሕወሓት ትጥቅ መፍታት ጎን ለጎን የኢትዮጵያን መሬት ለቆ እንደሚወጣ ቢሰፍርም፤ አሁንም ሙሉ ለሙሉ እንዳልወጣ ከቀናት በፊት የሕወሓት አመራሩ ጌታቸው ረዳ ተናግረዋል፡፡ ጦሩ በኢትዮጵያ ቆይታው በትግራይ ክልል በበርካታ የሰብብዊ መብቶች ጥሰት ውንጀላ የሚቀርብበት ነው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img