Sunday, September 22, 2024
spot_img

የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ በሱዳን ቆይታቸው በአራት ጉዳዮች ላይ ከአገሪቱ ባለሥልጣናት ጋር እንደሚመክሩ ተነገረ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ሚያዝያ 27፣ 2013 ― በትላንትናው እለት ለሁለት ቀናት ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ወደ ካርቱም ያቀኑት የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ በአገሪቱ ቆይታቸው በአራት ጉዳዮች ላይ ከሱዳን ባለሥልጣናት ጋር ይመክራሉ የተባለ ሲሆን፣ ከነዚህ አራት ጉዳዮች መካከል ሁለቱ ኢትዮጵያ እና ሱዳን የገቡበትን የድንብር ውጥረት የሚመለከትና በሕዳሴ ግድብ ላይ መሆኑን የሱዳን ሚዲያዎች ይዘዋቸው የወጡ ዘገባዎች አመልክተዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ ከነዚህ ጉዳዮች ውጭ ሦስቱን አገራት ማለትም ኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ኤርትራን በሚያዋስነው ድንበር በተመለከተ እንዲሁም የኤርትራ አማጺያንን አስመልክቶም ከሱዳን ባለሥልጣናት ጋር እንደሚነጋሩ ነው የተገለጸው፡፡

የኤርትራው ፕሬዝዳንት የሱዳን ጉብኝት የመጣው በተለይ በኢትዮጵያ እና ሱዳን መካከል እየከረረ የሚገኘው በአል ፋሻቃ ድንበር ላይ ውጥረት ላይ ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር አብራለች የሚል ሐሜት በሱዳኖቹ ዘንድ በመሰንዘሩ መሆኑን ታዛቢዎች እንደሚናገሩም ዘገባዎቹ አመልክተዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ የአሁኑ የሱዳን ጉብኝታቸው የቀድሞው የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ዑመር አልበሺር በመፈንቅለ መንግሥት ከሥልጣናቸው ከተሰናበቱ በኋላ ለሦስተኛ ጊዜ ያደረጉት መሆኑም ተነግሯል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img