Monday, October 7, 2024
spot_img

የአውሮፓ ኅብረት ምርጫ አልታዘብም ያለው “የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት የሚዳፈር ስራ ልስራ ብሎ ስላልተፈቀደለት” መሆኑን የውጭጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ሚያዝያ 26፣ 2013 ― ኅብረቱ ትላንት ባወጣው መግለጫ “ምርጫውን ለማካሄድ የሚያስችሉ ሁኔታዎች አልተሟሉም” በማለት ታዛቢ የመላክ እቅዱን መሰረዙን አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ በሰጡት መግለጫ የአውሮፓ ኅብረት በምርጫው ጉዳይ እንደማይታዘብ ያስታወቀው “የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት የሚዳፈር ስራ ልስራ ብሎ ስላልተፈቀደለት” ነው ብለዋል፡፡

አምባሳደር ዲና እንደገለጹት ኅብረቱ ምርጫ ሲታዘብ መጠቀም በሚፈልገው የመረጃ ቴክኖሎጂ እና የምርጫ ውጤት ከምርጫ ቦርድ ቀድሜ ይፋ ላድርግ የሚሉት ፋላጎቶቹ “የኢትዮጵያን ሉአላዊነት ስለሚፈታተን” ተቀባይነት እንደሌለው ገልጸዋል፡፡

የአውሮፓ ኅብረት ቀደም ሲል ባወጣው መግለጫ “ምርጫውን ለማካሄድ የሚያስችሉ ሁኔታዎች አልተሟሉም” በማለት ታዛቢ የመላክ እቅዱን ሰርዟል፡፡

የህብረቱ ከፍተኛ ተወካይ ጆሴፕ ቦሬል የአውሮፓ ህብረት ታዛቢዎች እንዲልክ በማሰብ ለመጪው የኢትዮጵያ ምርጫ አስፈላጊ ናቸው በተባሉ ቁልፍ መስፈርቶች ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ከስምምነት ለመድረስ ጥረት ሲያደረግ ቢቆይም አልተቻለም ብለዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img