አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ሚያዝያ 26፣ 2013 ― የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተሩ ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ድርጅቱን ለቀጣይ አምስት ዓመታት በድጋሚ በአለቃነት ለመምራት በሚያስችላቸው የሁለተኛ ዙር ውድድር ለመሳተፍ ፍላጎት እንዳላቸው የዘገበው ሬውተርስ ነው፡፡
በፈረንጆቹ ከ2017 ጀምሮ የዓለም ጤና ድርጅትን እየመሩ የሚገኙት ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም፣ በ2019 መገባደጃ ላይ የኮሮና ቫይረስ በማዕከላዊ ቻይናዊቷ ውሃን ከተማ መከሰቱን ተከትሎ የዓለም የጤና ድርጅት ኮቪድ19 ወረርሽኝን ለመታገል በሚያደርገው ትግል ጎልተው የወጡ መሆናቸው ይነገርላቸዋል፡፡
ዋና ዳይሬክተሩ ለሁለተኛ ዙር በሚያደርጉት ውድድር ከአፍሪካ ሀገራት ወሳኝ ድጋፍ እንደሚያገኙ ከወዲሁ ቢገመትም፣ ከሀገራቸው ኢትዮጵያ ድጋፍ ሊያገኙ ስለመቻላቸው ግን እርግጠኛ መሆን እንደማይቻል የዜና ወኪሉ ዲፕሎማቶች ነግረውኛል ብሏል፡፡
ዲፕሎማቶቹ ለዚህ እንደ ምክንያት ያስቀመጡት የኢትዮጵያ መንግሥት ዋና ዳይሬክተሩ በትግራይ ግጭት ጉዳይ ለቀድሞ ድርጅታቸው ሕወሀትን ወግነዋል በሚል በማለት መክሰሱን ነው፡፡
ለድርጅቱ የዋና ዳይሬክተርነት ቦታ የዓለም ጤና ድርጅት ከ194 አባል አገራቱ እስከ መጪው መስከረም እጪዎቻቸውን አሽገው ይልካ የተባለ ሲሆን፣ በዚሁ ሰበብ ከዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ጋር ተፎካካሪ የሚሆኑ ግለሰቦችን ማወቅ እንደማይቻልም ነው የተነገረው፡፡