Wednesday, December 4, 2024
spot_img

መንግሥት ጋዜጠኛ አበበ ባዩን ጨምሮ ሌሎችንም የሚዲያ ባለሞያዎች በአስቸኳይ ከእስር እንዲለቅ ሲፒጄ ጠየቀ

አምባ ዲጂታል፤ ሐሙስ ሰኔ 30 2014 የጋዜጠኞች መብት ተሟጋቹ ሲፒጄ መንግሥት ከቀናት በፊት በፀጥታ አካላት ከቤቱ የተወሰደውን ኢትዮ ፎረም የተሰኘው የበይነ መረብ ብዙኃን መገናኛ ዘጋቢ ጋዜጠኛ አበበ ባዩን ጨምሮ ሌሎችንም የሚዲያ ባለሞያዎች በአስቸኳይ ከእስር እንዲለቅ ጠይቋል፡፡

ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ሲፒጄ ይህን የጠየቀው ትላንት ረቡዕ ሰኔ 29 ባወጣው መግለጫው ላይ ነው፡፡ ሲፒጄ የጋዜጠኛውን የቅርብ ሰዎች ጠቅሶ እንዳሠፈረው፤ አበበ ሲቪል በለበሱ የፀጥታ አካላት ከመኖሪያ ቤቱ የተወሰደው ባለፈው ሳምንት ረቡዕ ሰኔ 22 ነው፡፡

አበበ ባዩ በፀጥታ አካላት ቁጥጥር ስር የዋለው የኢትዮ ፎረም ባልደረባው ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ በዋስትና ተለቆ በድጋሚ ከተያዘ ከአንድ ቀን በኋላ መሆኑም ነው የተገለጸው፡፡

የሥራ ባልደረቦቹ ያየሰው እና አበበ ከታሰሩ በኋላ ያሉበት እንዳልታወቀ ቢነገርም፤ አዲስ ስታንዳርድ ማክሰኞ ሰኔ 28 ይዞት በወጣው ዘገባ በአፋር ክልል አዋሽ አርባ እስር ቤት እንደሚገኝ ከተፈቺዎች ሰምቻለሁ ብሎ ነበር፡፡ ነገር ግን የጋዜጠኞች መብት ተሟጋቹ ሲፒጄ መረጃውን ማረጋገጥ እንዳልቻለ አመልክቷል፡፡ ያየሰው ሽመልስን በተመለከተ ግን አሁንም ድረስ ያለበትን እንዳልታወቀ ተነግሯል፡፡

የሲፒጄ ከሰሃራ በታች ያሉ የአፍሪካ ሀገራት ተወካዩ ሙቶኪ ሙሞ የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት አበበ ባዩን በዘፈቀደ ያሰሩ ሰዎችን ተጠያቂ እንዲያደርጉ ያሉ ሲሆን፣ የእርሱን እና የባልደረባውን መፈታትም ጠይቀዋል፡፡ 

ጋዜጠኞቹ ያየሰው ሽመልስ እና አበበ ባዩ ከወራት በፊት በተመሳሳይ በአዋሽ አርባ ታስረው መለቀቃቸው ይታወሳል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img