Thursday, December 5, 2024
spot_img

የኢትዮ ፎረሙ ጋዜጠኛ አበበ ባዩ በአዋሽ አርባ ታስሮ እንደሚገኝ ተነገረ

  • ባልደረባው ጋዜጠኛ አበበ ባዩ በአዋሽ አርባ እንደሚገኝ ተነግሯል

አምባ ዲጂታል፤ ማክሰኞ 28 2014 ኢትዮ ፎረም በተሰኘ የበይነ መረብ ብዙኃን መገናኛ አዘጋጅ የሆነው ጋዜጠኛ አበበ ባዩ በጸጥታ አካላት ከቤቱ ተወስዶ በአፋር ክልል አዋሽ አርባ እንደሚገኝ ተነግሯል፡፡

አዲስ ስታንዳርድ በድረ ገጹ የጋዜጠኛውን የቅርብ ቤተሰብ ጠቅሶ እንደዘገበው፤ አበበ ከመኖሪያ ቤቱ በፀጥታ ኃይሎች ከተወሰደ በኋላ በአዋሽ አርባ እንደሚገኝ የተሰማው ከተፈቺዎች ነው፡፡

ጋዜጠኛ አበበ ባዩ ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ በአዋሽ አርባ ከሌሎች ጋዜጠኞች ጋር ታስሮ መቆየቱ ይታወቃል፡፡

በተያያዠ መረጃ ሌላኛው የኢትዮ ፎረም ባልደረባ ያየሰው ሽመልስ በድጋሚ በፀጥታ አካላት ከቤቱ ከተወሰደ በኋላ የደረሰበት አለመታወቁን ቤተሰቦቹ ገልጸዋል፡፡ ጋዜጠኛው ግንቦት 18፣ 2014 በፖሊስ ቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ በእስር ቆይቶ በአስር ሺሕ ብር ዋስትና የተለቀቀ ቢሆንም፤ ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ ሰኔ 20 በድጋሚ ሲቪል በለበሱ የፀጥታ አካላት መወሰዱ ተነግሮ ነበር፡፡

ድረ ገጹ ይዞት በወጣው መረጃ ያየሰው ሽመልስ በድጋሚ በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ ቤተሰቦቹ የደረሰበትን ማወቅ አልቻልንም እንዳሉት አስነብቧል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img