Sunday, October 6, 2024
spot_img

ግብጽ ከፈረንሳይ 30 ዘመናዊ የጦር ጄቶችን ልትገዛ ነው ተባለ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ሚያዝያ 26፣ 2013 ― ግብጽ 4 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ዋጋ ያላቸው 30 የጦር ጄቶችን ከፈረንሳይ ለመግዛት ከስምምነት ላይ መድረሷን የአገሪቱ የመከላከያ ሠራዊት መገለጹን ሬውተርስ ዘግቧል፡፡

ለግብጽ 30 የራፋል የጦር ጀቶችን ሊሸጥ ተስማምቷል የተባለው ፈረንሳይ የሚገኘው ዳሳውልት አቪዬሽን ሲሆን፣ ግብጽ የጄቶቹን ጠቅላላ ዋጋ ማለትም 4 ነጥብ 5 ቢልዮን ዶላር ክፍያ በአስር ዓመት ለመክፈል መስማማቷ ነው የተገለጸው፡፡

የሁለቱ አገራት የጦር ጄት ግዢ ስምምነት እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በፈረንጆቹ 2021 ሚያዝያ መጨረሻ ላይ መደረጉን ምሥጢራዊ ሰነዶችን ዋቢ አድርጎ ያመለከተው ዘገባው፣ የግብፅ ልዑካን በዛሬው እለት ፓሪስ ሲደርሱ የሽያጩ በውልና ስምምነት ሊከናወን እንደሚልችም ተነግሯል፡፡

ግብፅ የምትገዛው ጄት በሰአት 1 ሺሕ 389 ኪሎ ሜትር እንደሚጓዝ የተነገረለት ሲሆን፣ ክብደቱ 9 ሺሕ 979 ኪሎ ግራም ሲመዝን፣ የክንፍ ስፋቱ ደግሞ 11 ሜትር ነው።

አንዳንድ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች አንደዚህ ያለውን መሳሪያ ለግብፅ መሸጥ በአገሪቱ ብዙ የሰብአዊ መብት ረገጣ እየፈፀመ ያለውን መንግሥት ማበረታት ነው በማለት ፈረንሳይን የኮነኑ ቢሆንም፣ የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በታኅሣሥ ወር ግብጽ በቀጣናው ሽብርተኝነትን ስለምትመክት መዳከም እንደሌለባት በመጥቀስ አገራቸው የጦር መሣሪያዎችን ለመሸጥ ቅድመ ሁኔታዎችን እንደማያስቀምጡ መናገራቸውንም ዘገባው አስታውሷል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img