Sunday, October 6, 2024
spot_img

በትግራይ ክልል ደቡባዊ ዞን የሚሠጠውን እርዳታ ከማይጨው ማሻገር እንዳልቻለ የተባበሩት መንግሥታት እርዳታ ማስተባበሪያ ቢሮ ገለጸ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ሚያዝያ 25፣ 2013 ― በትግራይ ክልል ደቡባዊ ዞን የሚሰጠው እርዳታ ከማይጨው ሊሻገር እንዳልቻለ የተባበሩት መንግሥታት እርዳታ ማስተባበሪያ ቢሮ ባወጣው ወቅታዊ ሪፖርት አመልክቷል፡፡

ቢሮው አሁን ባወጣው ሪፖርት የሰብአዊ እርዳታ አቅራቢዎች ሪፖርቱ ያመለክታል ካለበት ከሚያዝያ 9 እስከ ሚያዝያ 15 ድረስ በነበረው ጊዜ የሰብአዊ እርዳታ አቅራቢዎች ከማይጨው አልፈው መጓዝ ባለመቻላቸው የኦፍላ እና ነግሰጌ ወረዳዎችን መድረስ እንዳልቻሉ አሳውቋል፡፡

በተጨማሪም ቢሮው የመቀለ አቢ አዲ እና ሽሬ መንገድ በጸጥታ ስጋት ሰበብ ዝግ እንደሆነበትም ገልጧል፡፡

ስድስት ወራት ባስቆጠረው የትግራይ ክልል ግጭት የመገናኛ አገልግሎቶች የመረጥ ችግር ስለሚስተዋል በሰሜን ምእራብ፣ በማእከላዊ እና ምሥራቅ ትግራይ አንዳንድ አካባቢዎች እንዲሁም በደቡባዊ ምሥረቅ ዞኖች የሚላኩ የሰብአዊ አቅርቦቶችን በተመለከተ ሪፖርቶች እየዘገዩበት መሆኑንም አሳውቋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img