Sunday, November 24, 2024
spot_img

ኢትዮጵያ በበርበራ ወደብ ላይ ያላትን ድርሻ አጥታለች የሚባልበት ደረጃ አለመድረሱን አቶ አሕመድ ሽዴ ገለጹ

አምባ ዲጂታል፤ ሰኞ ሰኔ 06 2014 ኢትዮጵያ በ2010 ከዱባዩ ዲፒ ወርልድ እና ከሶማሌላንዱ ጋር የተጋራችውን የበርበራን ወደብ 19 በመቶ ድርሻ አጥታዋለች የሚባልበት ደረጃ ላይ እንዳልደረሰች የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አሕመድ ሽዴ ገልጸዋል፡፡

ካፒታል ጋዜጣ እንደዘገበው፣ የወደቡን ባለቤትነት በተመለከተ ንግግሮች አሁንም እንደቀጠሉ እና ተጨማሪ ሥራዎች የሚቀሩ እንዳሉ ገልፀው፤ ኢትዮጵያ ባለቤትነቷን አጥታለች የሚባልበት ደረጃ አልደረሰም፡፡

የኢትዮጵያ የበርበራ ወደብ ድርሻ ማጣት ዜና የመጣው የሶማሊላንድ የገንዘብ ሚኒስትር የአገሪቱ መንግስት የባለቤትነት መብትን አስመልክቶ ያስቀመጠውን ቅድመ ሁኔታ ኢትዮጵያ ማሟላት ባለመቻሏ በበርበራ ወደብ ላይ የ19 በመቶ ድርሻዋን አጥታለች ብለው ነበር።

በ2010 በተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች በተፈረመው የበርበራ ወደብ ሥምምነት መሠረት ኢትዮጵያ 19 በመቶ ድርሻ ስትወስድ፣ ዲ ፒ ወርልድ የተባለው ዓለም አቀፍ የወደቦች አስተዳዳሪ ኩባንያ 51 በመቶ እና የሶማሌላንድ መንግሥት ደግሞ ቀሪውን 30 በመቶ ድርሻ ወስደዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img