Thursday, December 5, 2024
spot_img

አምስት የትግራይ ቴሌቪዥን ጋዜጠኞች ‹‹ከጠላት ጋር ተባብራችኋል›› ተብለው ታሠሩ

አምባ ዲጂታል፤ ዐርብ ሰኔ 03 2014 ― አምስት የትግራይ ቴሌቪዥን ጋዜጠኞች ከጠላት ጋር ተባብራችኋል ተብለው መታሠራቸው ተሰምቷል፡፡ መታሠራቸው የተገለጸው ጋዜጠኞች እና የክልሉ ቴሌቪዥን ሌሎች ባልደረቦች ተሾመ ጠማለው፣ ምሥግና ሥዩም፣ ሐብን ሐለፎም፣ ኃይለሚካኤል ገሠሠ እና ዳዊት መኮንን የተባሉ ናቸው፡፡

ስለ ጉዳይ ለአሜሪካ ድምጽ የተናገሩት የሐብን ሐለፎም ጠበቃ ደንበኛቸው ከጠላት ጋር ተባብረሃል ተብሎ እንደታሠረ የገለጹ ሲሆን፣ ጠላት የተባለው ብልጽግና ፓርቲ ሊሆን እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡

ከታሳሪዎቹ መካከል ተሾመ ጠማለው፣ ምሥግና ሥዩም እና ኃይለሚካኤል ገሠሠ 12 ቀናት በእስር ማሳለፋቸው ሲነገር፣ ዳዊት መኮንን ደግሞ አምስት ቀናት በእስር ቤት ቆይቷል፡፡ በነዚህ ጋዜጠኞች ላይ እስካሁን ድረስ አቃቤ ሕግ ክስ እንዳልመሠረተባቸው ነው የተገለጸው፡፡ 

ሆኖም የመቀሌ ከተማ አቃቤ ሕግ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አዲስ ገብረሥላሴ ግለሰቦቹ “የታሰሩት በጋዜጠኛነት ሞያቸው ምክንያት ሳይሆን ከሞያው ውጭ በወንጀል ተጠርጥረው ነው” ብለዋል፡፡  

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img