Sunday, November 24, 2024
spot_img

ኢትዮጵያ የበርበራ ወደብ 19 በመቶ ድርሻዋን ማጣቷ ተዘገበ

  • መንግሥት እስካሁን በጉዳዩ ላይ ምላሽ አልሰጠም

አምባ ዲጂታል፤ ዐርብ ሰኔ 03 2014 ኢትዮጵያ የሶማሌላንዱን በርበራ ወደብ 19 በመቶ ድርሻ ወደቡን ከሚያስተዳድረው የዱባዩ ዲ ፒ ወርልድ ኩባንያ ጋር በ2010 መጋራቷ ይታወሳል፡፡

በወቅቱ በተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች በተፈረመው ሥምምነት መሠረት ኢትዮጵያ 19 በመቶ ድርሻ ስትወስድ፣ ዲ ፒ ወርልድ የተባለው ዓለም አቀፍ የወደቦች አስተዳዳሪ ኩባንያ 51 በመቶ እና የሶማሌላንድ መንግሥት ደግሞ ቀሪውን 30 በመቶ ድርሻ ወስደዋል፡፡

ሪፖርተር በድረ ገጹ ሥማቸው ያልተገለጸ የራስ ገዟን ሶማሊላንድ ባለሥልጣን ጠቅሶ እንደዘገበው፤ ኢትዮጵያ በወቅቱ የተካፈለችውን ድርሻ አሁን አጥታለች፡፡

እንደ ዘገባው ከሆነ ኢትዮጵያ ድርሻውን ያጣችው በወቅቱ የተደረገውን ስምምነት ለማጠናቀቅ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ የሚያስፈልጉ ነገሮችን ባለማሟላቷ ነው፡፡ ይህንኑ ተከትሎ ኢትዮጵያ ያጣችው 19 በመቶ ድርሻ ወደ ዲ ፒ ወርልድ እና ሶማሊላንድ የሚተላለፍ ይሆናል ነው የተባለው፡፡

ኢትዮጵያ በ2010 ከወደቡ ድርሻ ለመጋራት ስምምነት ስትፈጽም፤ የበርበራ ወደብን ለገቢ እና ወጪ ንግዷ ለመጠቀም የሚያስችላትን መሠረተ ልማት እንደምታለማ ተገልጾ የነበረ ሲሆን፣ ባለፈው ዓመት ሰኔ ወር ላይ ደግሞ የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ጊቤ የሚል ሥያሜ ያላት የኢትዮጵያ መርከብ በወደቡ ላይ መሠማራቷን አስታውቆ ነበር፡፡

አሁን ኢትዮጵያ አጥታዋለች የተባለውን የበርበራን ወደብ በተመለከተ እስካሁን ድረስ ከመንግሥት በኩል ምላሽ አልተሰጠበትም፡፡

አሁን መቅሩቱ በተነገረው የበርበራ ወደብ ድርሻ ጉዳይ ስምምነቱ በተፈጸመበት ወቅት የሶማሊያ መንግሥት ፓርላማ ተቃውሞ አቅርቦበት ነበር፡፡ የወቅቱ የሶማሊያ ፓርላማ ለቅሬታው ያስቀመጠው ምክንያት ሉአላዊነታችን ተነክቷል የሚል እንደነበርም ይታወሳል፡፡ በአንጻሩ የራስ ገዟ የሶማሌላንዱ ፓርላማ ግን ወዲያውኑ ስምምነቱን አፅድቆት ነበር፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img