Sunday, October 6, 2024
spot_img

በአዲስ አበባ የኮሮና መስፋፋትን ለመቀነስ አዲስ የትራንስፖርት መመሪያ ነገ ይፋ ይደረጋል ተባለ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ሚያዝያ 25፣ 2013 ― የኮሮና ቫይረስ መስፋፋትን ተከትሎ በአዲስ አበባ ከተማ አዲስ መመሪያ መዘጋጀቱን የከተማዋ ትራንስፖርት ቢሮ ገልጿል።

የቢሮው የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ አቶ አረጋዊ ማሩ ነግረውኛል ብሎ አል እንደዘገበው በአዲስ አበባ እየተስፋፋ የመጣውን የኮሮና ቫይረስ ለመቀነስ የትራንስፖርት ቢሮ አዲስ መመሪያ አዘጋጅቷል፡፡

የቫይረሱን ሥርጭት ለመከላከል ከዚህ በፊት የተሽከርካሪዎችን የመጫን አቅም መወሰን፤ የታሪፍ መጠን ላይ ማሻሻያ ማድረግ፤ አውቶሞቢሎን በሙሉ እና በጎዶሎ ቁጥር ማሰማራት እና ሌሎች ስራዎች በቢሮው መመሪያዎች ተዘጋጅተው ሲተገበሩ ቆይተዋል።

ይሁንና የቫይረሱ ስርጭት አሁን ላይ እየጨመረ በመምጣቱ አዲስ የትራንስፖረት መመሪያ መዘጋጀቱን ኃላፊው ገልጸዋል፡፡

የመመሪያው ሙሉ ይዘት በነገው ዕለት ለሕዝብ ይፋ እንደሚደረግም ነው የተነገረው፡፡

በአገሪቱ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ከመጋቢት ጀምሮ እስከ ነሐሴ 2012 ድረስ ለአምስት ወራት በቆየ አዋጁ መሰረት ታክሲዎች በግማሽ እንዲጭኑ ሲደረግ፣ ታክሲዎች በግማሽ እንዲጭኑ ተሳፋሪዎች የመጀመኛውን ታሪፍ እጥፍ ሲከፍሉ እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img