አምባ ዲጂታል፤ ዐርብ ግንቦት 26፣ 2014 ― የፌዴራል መንግሥት ባለፉት ቀናት እየወሰደ የሚገኘው እርምጃ ሦስት አካላትን ኢላማ ያደረገ መሆኑን ይፋ አድርጓል፡፡
የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ሚኒስትሩ ዶክተር ለገሠ ቱሉ እንደገለጹት በተለይ በአማራ ክልል በመጀመሪያ ደረጃ መንግሥት እርምጃውን እየወሰደ የሚገኘው ከተለያዩ እስር ቤቶች በማምለጥ የራሱን አደረጃጀት ፈጥሮ ከመንግሥት የፀጥታ አካላት ጋር የሚገዳደር ኃይል ነው ብለዋል፡፡ ሌላኛው ከሕገ ወጥ የጦር መሣሪያ እና ከኮንትሮባንድ ጋር ትስስር ፈጥረው ይህንኑ በትጥቅ ማከናወን ከሚፈልግ ኃይል ነው ያሉት ሚኒስትሩ፣ ቀሪው ቡድን በመንግሥት ፀጥታ መዋቅር ውስጥ የነበረና ፀረ መንግስት እንቅስቃሴ ያደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ዶክተር ለገሠ የብልጽግና ፓርቲ ንብረት ከሆነው ፋና ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ አሁን መንግሥት እየወሰደ የሚገኘው ‹‹ሕግ ማስከበር›› ሲሉ የጠሩት እርምጃ ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ከኅብረተሰቡ ጋር በተደረገ ውይይት በአንገብጋቢነት ሲጠየቅ የነበረ ነው ብለዋል፡፡
መንግሥት ከሰሞኑ በወሰደው እርምጃ የቀድሞው የአማራ ክልል ልዩ ኃይል አዛዥ ሌተናል ኮሎኔል ተፈራ ማሞን ጨምሮ በርካታ የመገናኛ ብዙኃን ባለሞያዎች እና ፋኖ የተሰኘውን መደበኛ ያልሆነ ቡድን አባላትን በቁጥጥር ስር አውሏል፡፡
እንደ ኮሚኒኬሽን ሚኒስትሩ ከሆነ በአሁኑ ጊዜ እርምጃው እየተወሰደ የሚገኘው በአማራ፣ በኦሮሚያ እና ባለፈው ዓመት በተመሠረተው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልሎች መሆኑን ዘርዝረዋል፡፡
ዶክተር ለገሠ በቆይታቸው አሁን በተለይ በአማራ ክልል ያለውን ሁኔታ አንስተዋል፡፡ መንግስት ከሕወሓት ጋር ባካሄደው ጦርነት በርካቶች መሰለፋቸውን አስታውሰው፣ በአማራ ክልል ተሳትፎ ያደረጉት ሁሉም ኃይሎች እውቅና እንደተሰጣቸውና በተለየ ሁኔታ የሚበተን ወይም ሌላ እርምጃ የሚወሰድበት እንደሌለ ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም ሚኒስትሩ በአገሪቱ ከአንድ ክልል ወደ ሌላ መንቀሳቀስ የማይቻልበት ሁኔታ ተፈጥሮ ነበር ያሉ ሲሆን፣ አሁን በቁጥጥር ስር የዋሉ ግለሰቦች መንግሥትን በመተቸታቸው ብቻ የታሰሩ እንዳልሆኑም ገልጸዋል፡፡
ከዚሁ ጋር አያይዘው ከታሰሩት ሰዎች በላይ መንግስትን የሚተቹ ሰዎች መኖራቸውን በመጥቀስ፣ አሁን በመንግስት እየተደረገ የሚገኘው ከሽብር ቡድኖች ጋር እና ሥርዐት አልበኝነት ለመፍጠር ከሚያንቀሳቀሱ ኃይሎች ጋር ትስስር ያላቸውን በቁጥጥር ስር ማዋር ነው ብለዋል፡፡
ዶክተር ለገሠ እነዚህ ግለሰቦች አንድ ህብረተሰብ በሌላው ላይ እንዲነሳ ከማድረግ በተጨማሪ በትጥቅ ጭምር አንዱ አካባቢ ሌላው ላይ እንዲዘምት ተንቀሳቅሰዋል ሲሉ ወንጅለዋል፡፡ አንዳንዶቹን መንግስት ማስጠንቀቂያ ጭምር ሰጥቷቸው እንደነበር አስታውሰው፤ ‹‹ታጋሽነቱን እንደ ድክመት ቆጥረው›› መንቀሳቀሳቸውን ተናግረዋል፡፡
ከሰሞኑ በተወሰደው እርምጃ ከሌሎች ግለሰቦች በተጨማሪ 18 የመገናኛ ብዙኃን አባላት በቁጥጥር ስር የዋሉ ውለዋል፡፡ ከታሰሩት መካከል የፍትሕ መጽሔት ማኔጂንግ ዳይሬክተሩ ተመስገን ደሳለኝ፣ በበይነ መረብ የሚሠሩት ያየሰው ሽመልስ፣ መስከረም አበራ፣ መዐዛ መሐመድ እና ሰለሞን ሹምዬ ይገኙበታል፡፡ ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ የሚገኘውን እነዚህን ባለሞያዎች ፖሊስ “ሁከት እና ብጥብጥ በማነሳሳት” ጠርጥሬያቸዋለሁ ብሏል፡፡
መንግሥት እርምጃ እየወሰድኩባቸው ነው ያላቸውን ሦስት አካላት ይፋ አደረገ
አምባ ዲጂታል፤ ዐርብ ግንቦት 26፣ 2014 ― የፌዴራል መንግሥት ባለፉት ቀናት እየወሰደ የሚገኘው እርምጃ ሦስት አካላትን ኢላማ ያደረገ መሆኑን ይፋ አድርጓል፡፡
የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ሚኒስትሩ ዶክተር ለገሠ ቱሉ እንደገለጹት በተለይ በአማራ ክልል በመጀመሪያ ደረጃ መንግሥት እርምጃውን እየወሰደ የሚገኘው ከተለያዩ እስር ቤቶች በማምለጥ የራሱን አደረጃጀት ፈጥሮ ከመንግሥት የፀጥታ አካላት ጋር የሚገዳደር ኃይል ነው ብለዋል፡፡ ሌላኛው ከሕገ ወጥ የጦር መሣሪያ እና ከኮንትሮባንድ ጋር ትስስር ፈጥረው ይህንኑ በትጥቅ ማከናወን ከሚፈልግ ኃይል ነው ያሉት ሚኒስትሩ፣ ቀሪው ቡድን በመንግሥት ፀጥታ መዋቅር ውስጥ የነበረና ፀረ መንግስት እንቅስቃሴ ያደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ዶክተር ለገሠ የብልጽግና ፓርቲ ንብረት ከሆነው ፋና ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ አሁን መንግሥት እየወሰደ የሚገኘው ‹‹ሕግ ማስከበር›› ሲሉ የጠሩት እርምጃ ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ከኅብረተሰቡ ጋር በተደረገ ውይይት በአንገብጋቢነት ሲጠየቅ የነበረ ነው ብለዋል፡፡
መንግሥት ከሰሞኑ በወሰደው እርምጃ የቀድሞው የአማራ ክልል ልዩ ኃይል አዛዥ ሌተናል ኮሎኔል ተፈራ ማሞን ጨምሮ በርካታ የመገናኛ ብዙኃን ባለሞያዎች እና ፋኖ የተሰኘውን መደበኛ ያልሆነ ቡድን አባላትን በቁጥጥር ስር አውሏል፡፡
እንደ ኮሚኒኬሽን ሚኒስትሩ ከሆነ በአሁኑ ጊዜ እርምጃው እየተወሰደ የሚገኘው በአማራ፣ በኦሮሚያ እና ባለፈው ዓመት በተመሠረተው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልሎች መሆኑን ዘርዝረዋል፡፡
ዶክተር ለገሠ በቆይታቸው አሁን በተለይ በአማራ ክልል ያለውን ሁኔታ አንስተዋል፡፡ መንግስት ከሕወሓት ጋር ባካሄደው ጦርነት በርካቶች መሰለፋቸውን አስታውሰው፣ በአማራ ክልል ተሳትፎ ያደረጉት ሁሉም ኃይሎች እውቅና እንደተሰጣቸውና በተለየ ሁኔታ የሚበተን ወይም ሌላ እርምጃ የሚወሰድበት እንደሌለ ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም ሚኒስትሩ በአገሪቱ ከአንድ ክልል ወደ ሌላ መንቀሳቀስ የማይቻልበት ሁኔታ ተፈጥሮ ነበር ያሉ ሲሆን፣ አሁን በቁጥጥር ስር የዋሉ ግለሰቦች መንግሥትን በመተቸታቸው ብቻ የታሰሩ እንዳልሆኑም ገልጸዋል፡፡
ከዚሁ ጋር አያይዘው ከታሰሩት ሰዎች በላይ መንግስትን የሚተቹ ሰዎች መኖራቸውን በመጥቀስ፣ አሁን በመንግስት እየተደረገ የሚገኘው ከሽብር ቡድኖች ጋር እና ሥርዐት አልበኝነት ለመፍጠር ከሚያንቀሳቀሱ ኃይሎች ጋር ትስስር ያላቸውን በቁጥጥር ስር ማዋር ነው ብለዋል፡፡
ዶክተር ለገሠ እነዚህ ግለሰቦች አንድ ህብረተሰብ በሌላው ላይ እንዲነሳ ከማድረግ በተጨማሪ በትጥቅ ጭምር አንዱ አካባቢ ሌላው ላይ እንዲዘምት ተንቀሳቅሰዋል ሲሉ ወንጅለዋል፡፡ አንዳንዶቹን መንግስት ማስጠንቀቂያ ጭምር ሰጥቷቸው እንደነበር አስታውሰው፤ ‹‹ታጋሽነቱን እንደ ድክመት ቆጥረው›› መንቀሳቀሳቸውን ተናግረዋል፡፡
ከሰሞኑ በተወሰደው እርምጃ ከሌሎች ግለሰቦች በተጨማሪ 18 የመገናኛ ብዙኃን አባላት በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡ ከታሰሩት መካከል የፍትሕ መጽሔት ማኔጂንግ ዳይሬክተሩ ተመስገን ደሳለኝ፣ በበይነ መረብ የሚሠሩት ያየሰው ሽመልስ፣ መስከረም አበራ፣ መዐዛ መሐመድ እና ሰለሞን ሹምዬ ይገኙበታል፡፡ ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ የሚገኘውን እነዚህን ባለሞያዎች ፖሊስ “ሁከት እና ብጥብጥ በማነሳሳት” ጠርጥሬያቸዋለሁ ብሏል፡፡