Sunday, October 6, 2024
spot_img

ሒጅራ ባንክ በቀጣይ ሦስት ወራት ወደ ሥራ እንደሚገባ አስታወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ሚያዝያ 25፣ 2013 ― ከወለድ ነፃ ባንክ አገልግሎት ለመስጠት በተለያየ ደረጃ ላይ ሆነው በዝግጅት ላይ ከሚገኙ ወደ ስድስት ከሚሆኑ ከወለድ ነፃ ባንኮች መካከል አንዱ የሆነው ሒጅራ ባንክ፣ በሦስት ወራት ውስጥ ወደ ሥራ እንደሚገባ ያስታወቀው ለዋና መሥሪያ ቤትነት የሚገለገልበትን ሕንፃ ገብቶ ማስመረቁንና የመጀመርያውን የባንኩን ፕሬዚዳንት መሰየሙን ባስታወቀበት ወቅት ነው፡፡

በባንክ ኢንዱስትሪ ውስጥ ባልተለመደ ሁኔታ ሥራ ከመጀመሩ በፊት የራሱ ሕንፃ መግዛቱን ያስታወቀው ሒጅራ ባንክ፣ ባለ ዘጠኝ ወለል ሕንፃውን ባለፈው ሳምንት ረቡዕ ሚያዝያ 20 2013 አስመርቋል፡፡

ሕንፃውን 130 ሚሊዮን ብር ወጪ አድርጎ የገዛው መሆኑንም የሒጅራ ባንክ የዳሬክተሮች ቦርድ ሊቀመንበር አቶ ሙከሚል በድሩ ገልጸዋል፡፡ ይኸው ባንክ በባንክ ኢንዱስትሪ ውስጥ ረዥም ዓመት ልምድ እንዳላቸው የሚነገርላቸውን አቶ ዳዊት ቀኖ አባገሮን በመምረጥ የመጀመርያው የሂጅራ ባንክ ተቀዳሚ ፕሬዚዳነት አድርጎ ሾሟል፡፡

ሒጅራ ባንክ ከዘጠኝ ሺሕ በላይ ባለአክሲዮኖች ያሉት ሲሆን፣ የተፈከለ ካፒታሉ ደግሞ 700 ሚሊዮን ብር እንደሆነ ተነግሯል፡፡ ከዚህ ውስጥ የተለያዩ ተቀናሾች ወጥተው የተከፈለ ካፒታሉ 560 ሚሊዮን ብር እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡

ባንኩ ካለው የተከፈለ 1 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ካፒታል አንፃር በቅርቡ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የወጣው መመርያ ባንኮች የተከፈለ ካፒታላቸውን 5 ቢሊዮን ብር እንዲያደርሱ መወሰኑን ከሒጅራ ባንክ እንዴት ያየዋል የሚል ጥያቄ የቀረበ ቢሆንም፣ የባንኩ ቦርድ ሰብሳቢ ባንካቸው በተጠቀሰው ጊዜ አምስት ቢሊዮን ብር ካፒታሉን የሚያሟላ ስለመሆኑ መናገራቸውን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img