Saturday, November 23, 2024
spot_img

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ለሚገኙ አርሶ አደሮች የመሬት ባለቤትነት የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ተሰጣቸው

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ሚያዝያ 23፣ 2013 ― በክፍለ ከተማው ለሚገኙ 600 አርሶ አደሮች የመሬት ባለቤትነት የይዞታ ማረጋገጫ ካርታውን ያስረከቡት የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ናቸው፡፡

በዚሁ ሥነ ሥርዐት ላይ አርሶ አደሩ በራሱ መሬት እና እርሻ ላይ ሰርቶ የመለወጥ መብቱ ሊረጋገጥለት እና ሊከበርለት ይገባል ያሉት ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፣ በደላሎችም ሆነ በሕገ ወጥ መሀንዲሶች የሚደረግ ዘረፋ ሊቆም ይገባል ማለታቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ጽሕፈት ቤት በፌስቡክ ገጹ ላይ አሳውቋል፡፡

ዛሬ በክፍለ ከተማው የባለቤትነት የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ የተሰጣቸው አርሶአደሮች ተገቢውን ልማት በማካሄድ ከራሳቸው አልፈው ለከተማዋ ልማት ሊሰሩ እንደሚገባም ምክትል ከንቲባዋ ተናግረዋል ነው የተባለው፡፡

በቀጣይም በሌሎች ክፍለ ከተሞች ለሚገኙ አርሶአደሮች የባለቤትነት የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ የመስጠት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img