Sunday, October 6, 2024
spot_img

በቤንች ሸኮ ዞን ታጣቂዎች ስድስት ሰዎችን መግደላቸው ተሰማ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ሚያዝያ 23፣ 2013 ― በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል ቤንች ሸኮ ዞን ዳንቹ ቀበሌ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት ስድስት ንጹሐን ሰዎች መገደላቸው ተሰምቷል፡፡

በጥቃቱ ከተገደሉት መካከል ቤታቸው ውስጥ ባሉበት በአሰቃቂ ሁኔታ የተቃጠሉ ሰዎች እንደሚገኙበትም አዲስ ስታንዳርድ ዘግቧል፡፡

በዞኑ ጉራፈርዳ ወረዳ ባለፈው ወር በተመሳሳይ ቢያንስ 10 ሰዎች በታጣቂዎች መገደላቸውንም ዘገባው አስታውሷል፡፡ በወቅቱ ጥቃቱ የደረሰባቸው ጌልማ፣ ጌሊቲ እና ሙልሙል በተባሉ ቀበሌዎች ነበር፡፡

ታጣቂዎቹ ጥቃቶቹን ካደረሱ በኋላ በደቡብ ሱዳንና በጋምቤላ ክልል አዋሳኝ በሆኑ የድንበር አካባቢዎች ውስጥ ገብተው በመሸሸግ ተመልሰው እየመጡ ጥቃት እንደሚፈጽሙ የደቡብ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አለማየሁ ባውዴ ለሚዲያዎች ተናግረው ነበር፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img