Sunday, September 22, 2024
spot_img

ባልደራስ ምርጫ ቦርድን እከሳለሁ አለ

አምባ ዲጂታል፤ ሐሙስ መጋቢት 1 2014 ― ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራራ ፓርቲ (ባልደራስ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድን የሚከሰው ከአዲስ አበባ ምክር ቤት አባሉ የብልጽግና ሰው አቶ ዘላለም ሙላቱ ጉዳይ ጋር በተገናኘ ነው፡፡

ባልደራስ የካቲት 7፣ 2014 ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በጻፈው ደብዳቤ፣ የአዲስ አበባ ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ዘላለም ሙላቱን ከምክር ቤት ለማስነሳት ድጋፍ እንዲደረግለት ያቀረበውን ቅሬታ ውድቅ መደረጉ ይታወቃል፡፡

ፓርቲው በእለቱ በጻፈው ደብዳቤ አቶ ዘላለም የካቲት 3፣ 2014 በአዲስ አበባ ምክር ቤት ባሰሙት ንግግር ‹‹በኦሮሚያ ል ዞን ስር የሚገኙ አካባቢዎች አዲስ አበባ ከርሷን ሞልታ ፈርሷን የምትጥልባቸው ናቸው›› ማለታቸው በማስረጃ ስለተረጋገጠ፣ ከሕዝብ እንደራሴነታቸው የሚነሱበትንና የማሟያ ምርጫ የሚደረግበትን ሒደት ለማስጀመር ድጋፍ ይደረግልኝ ሲል ጠይቆ ነበር፡፡

ለዚሁ ጥያቄ ምርጫ ቦርድ የካቲት 14 2014 በሰጠው ምላሽ፣ የኢፌዴሪ ሕገ መንግስት መራጩ ሕዝብ አመኔታ በሚያጣበት ወቅት ተወካዩን ሊጠራ የሚችልበትን መብት ማረጋገጡን የገለጸ ሲሆን፣ አመኔታ ያጣው ተመራጭ ከመቀመጫው እንዲነሳ ሲደረግ ሕዝብ ውክልናውን መልሶ እንዲያገኝ የማሟያ ምርጫ እንደሚደረግ መደንገጉን አስታውሷል፡፡ ሆኖም ተመራጩ ይውረድልኝ የሚለው ሕዝብ መሆኑን ሕገ መንግስቱን ጠቅሶ አስገንዝቧል፡፡

በመሆኑም አግባብነት ባለው የሕግ ማዕቀፍ መሠረት በምርጫ ክልሉ ነዋሪ የሆነ መራጭ ሕዝብ ጥያቄውን ሲያቀርብ ቦርዱ መርምሮ ውሳኔ ከሚሰጥበትና በሰጠው ውሳኔ ላይ መሠረት በማድረግ ተወካዩ ተነስቶ የሟሟያ ምርጫ እንደሚያደርግ ያመለከተው ቦርዱ፣ ነገር ግን ከምክር ቤት መነሳትን በሚመለከት ለማንኛውም አካል በተለይም በምርጫ ክልሉ ተወዳዳሪ ለሆነ ፓርቲ ድጋፍ የሚያደርግበት የሕግ አግባብ ስለሌለ ባልደራስ ያቀረበውን ጥያቄ ተቀባይነት እንደሌለው አስታውቋል፡፡

ባልደራስ ትላንት ምሽት እንዳሳወቀው፣ አሁን በምርጫ ቦርድ ላይ ክሱን የሚመሰርተው የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የባልደራስ አባላትና ነዋሪዎች ባቀረቡት ጥያቄ መሠረት፣ አቶ ዘላለም ሙላቱን ከአዲስ አበባ ምክር ቤት ለማንሳት የሚያስችል ህጋዊ ቅጽ እንዲሰጠው ለምርጫ ቦርድ አቤቱታ አቅርቦ እንደነበር በማስታወስ፣ በብዙ ሺህዎች የሚቆጠሩ ፊርማዎች ተሰባስበው፤ “ያልተሟላ ነገር አለ” ተብሎ ውድቅ እንዳይሆን፣ የሚያስፈልጉ ነገሮችን ሁሉ ያሟላ ቅጽ ተዘጋጅቶ እንዲጠኝ ጠይቄያለሁ ነው ያለው፡፡

አያይዞም ምርጫ ቦርድ ሕጋዊ ቅጹን አዘጋጅቶ ለመስጠት ፍቃደኛ አለመሆኑን የገለጸው ፓርቲው፣ ሕጋዊ ቅጹ በምርጫ ቦርድ ተዘጋጅቶ እስካልቀረበ ድረስ ፊርማውን መሰብሰብ በከንቱ ሊሆን ስለሚችል፣ ወደ ፍርድ ቤት ሄዶ ምርጫ ቦርድ ቅጹን አዘጋጅቶ እንዲሰጠው ሕጋዊ ጥያቄ እንደሚያቀርብ አስታውቋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img