Sunday, November 24, 2024
spot_img

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ሕወሓት ባለበት አቋም የሚቀጥል ከሆነ መከላከያ ቡድኑን ለማጥፋት ወይም ተገዶ ወደ ድርድር እንዲመጣ የሚያስችለውን ሥራ እንደሚሠራ ተናገሩ


አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ የካቲት 21 2014 የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ ሕወሓት ባለበት አቋም የሚቀጥል ከሆነ መከላከያ ቡድኑን ለማጥፋት ወይም ተገዶ ወደ ድርድር እንዲመጣ የሚያስችለውን ሥራ እንደሚሠራ ተናግረዋል፡፡

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ይህንኑ የኢፌዴሪ አየር ኃይል ሥልጠናቸውን በብቃት ያጠናቀቁ የአየር ጥበቃ ፖሊስ አባላትና ቴክኒሻኖችን ባስመረቀበት ወቅት ገልጸዋል፡፡

በዋናነት በአየር ኃይል ላይ ባተኮረው ንግግራቸው፣ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑጁላ ከሕወሓት ጋር ስለነበረው ጦርነት አንስተዋል፡፡

በዚሁ ንግግር በጦርነቱ የጉዳቱ ሰለባ የሆነው የትግራይ ሕዝብ ነው ያሉት ፊልድ ማርሻሉ፣ በትግራይ ሕዝብ ላይ ደርሷል ያሉትን ጉዳት ‹‹ለመናገር የሚዘገንን›› ሲሉ ገልጸውታል፡፡

አያይዘውም ከመከላከያ ጋር ጦርነት ውስጥ የነበረው ሕወሓት፣ ስሕተት በስሕተት ላይ ጨምሮ እንዳይሄድ ጊዜ መስጠት አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሰው፣ ‹‹ከአሁን በኋላ በዚያ የሚቀጥሉ ከሆነ [ግን] ለማጥፋት ወይም ተገዶ ወደ ሰላም ለማምጣት የሚያስችል ወታደራዊ ሥራ ሁሉ እንሠራለን›› ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

ጨምረውም ‹‹በሕወሓት ላይ የተጀመረው ጦርነት አልተጠናቀቀም›› ብለዋል፡፡

ባለፈው ዓመት ጥቅምት ወር በትግራይ በጀመረውና ኋላም ወደ አማራ እና አፋር ክልሎች የተዛመተው የፌዴራል መንግስት እና ሕወሓት ጦርነት በቅርብ ጊዜያት በአንጻራዊነት ረገብ ማለቱ ይታወቃል፡፡

በሁለቱ አካላት መካከል ለሚደረገው ጦርነት ሰላማዊ መፍትሔ ለማበጀት ድርድር እየተካሄደ መሆኑ በሕወሓት መሪዎች እና በተመድ ኃላፊዎች በኩል ቢነገርም፣ ባለፈው ሳምንት ፓርላማ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ድርድር አለመጀመሩን ተናግረዋል፡፡ ነገር ግን ይህ ማለት ድርድር አይደረግም ማላት አይደለም ብለዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img