አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ሚያዝያ 22፣ 2013 ― በእስራኤል በ10 ሺሕ የሚቆጠሩ ሰዎች ተሳትፈውበታል በተባለ ዓመታዊ ክብር በአል ላይ ባጋጠመ የደረጃ መደርመስ በትንሹ 44 ሰዎች ሲሞቱ፣ ከ150 በላይ ሰዎች ቆስለው ከነዚህ መካከል 38 ሰዎች በከፋ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ተነግሯል፡፡
በሰሜናዊ ምሥራቅ የአገሪቱ ክፍል ሜሮን ተራራ ላይ የተካሄደው ክብር በዐል፣ ትላንት ሌሊቱን ሙሉ የቆየ መሆኑ ነው የተነገረው፡፡
አደጋው ተመልካቾች የቆሙበት ደረጃ ተደርምሶ እንደደረሰ ቢነገርም፣ የእስራኤል ቀይ መስቀል ግን የአደጋው ሰበብ መድረኩ ላይ ከፍተኛ ተመልካች በመገኘቱ እንደሆነ ገልጿል።
በአደጋው የቆሰሉ ሰዎችን በአምቡላንስ እና በሂልኮፕተር ወደ አራት ሆስፒታሎች መወሰዳቸውም ተገልጿል።
አደጋውን ተከትሎ ወደ ሥፍራው አቅንተዋል የተባለው የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ መጪውን እሑድ ብሔራዊ የሐዘን እንደሚሆን መናገራቸውን የወጡ ዘገባዎች አመልክተዋል፡፡