Sunday, October 6, 2024
spot_img

የዙሉዋ ንግሥት ሥልጣን በጨበጡ በአንድ ወራቸው ሕይወታቸው አለፈ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ሚያዝያ 22፣ 2013 ― በደቡብ አፍሪካ የዙሉ ጎሳ ንጉሣዊ ቤተሰብ ባለፈው ወር ሕይወታቸው ያለፈውን የባላቸው ንጉሥ ጉድዊል ዝዌሊቲኒን ሞት ተከትሎ ሥልጣኑን ተረክበው የነበሩት የ65 ዓመቷ ንግሥት ማንትፎምቢ ሥልጣን በያዙ በወራቸው እርሳቸውም ባላቸውን ተከትለው ሔደዋል፡፡

የንግሥቷን ኅልፈት ተከትሎም ህልፈታቸው እጅግ ያልተጠበቀ ስለነበር ቤተሰቡ ‹‹ክፉኛ ተጎድቷል›› እየተባለ ይገኛል፡፡

በጉዳዩ ላይ የተናገሩት የቤተሰቡ ሌላኛው አባል እና የንግሥቲቱ ጠቅላይ ሚኒስትር የሆኑት ልዑል ማንጎሱቱ ቡቴሌዚ የንግሥቱቷን ኅልፈት ለነገሩት የዙሉ ሕዝብ በቀጣይ ‹‹ምንም ዓይነት የሥልጣን ሽሚያ አይኖርም›› ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ንግሥት ማንትፎምቢ ወደ ሆስፒታል የገቡት ባለፈው ሳምንት እንደነበር የተገለጸ ሲሆን፣ ለሞት ያበቃቸው ህመም ምን እንደሆነ በይፋ እንደማይታወቅም የደቡብ አፍሪካ መገናኛ ብዙሃንን ዋቢ አድርጎ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

የዙሉን ጎሳ ለ50 ዓመታት በመግዛታቸው በአፍሪካ ረዥም ዓመት የነገሱ የሚል ስያሜ የነበራቸው የንጉሥ ጉድዊል ዝዌሊቲኒን ባለቤት ንግሥት ማንትፎምቢ ሥልጣን የተረከቡት መጋት 14፣ 2013 ነበር፡፡

ንግሥት ማንትፎምቢ ከንጉሥ ዝዌሊቲኒን ስምንት ልጆችን የወለዱ ሲሆን፣ ትልቁ ልጃቸው የ47 ዓመቱ ልዑል ሚሱዙሉ ሥልጣኑን ሊረከብ ይችላል የሚልግ ግምት መኖሩንም ዘገባው ጠቁሟል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img