Saturday, November 23, 2024
spot_img

የትግራይ ብልጽግና አባሉ በኦሮሞ ባህል መሠረት የብሔረሰብ አባል ሆኑ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ሚያዝያ 22፣ 2013 ― የብልጽግና ፓርቲ የትግራይ ቅርንጫፍ አባሉ ዶክተር አብርሃም በላይ በኦሮሞ ባህል መሠረት የብሔረሰቡ አባል መሆናቸው ተነግሯል፡፡

ለዶክተር አብርሃም በላይ በሞጋሳ ባህል መሠረት አዲስ ሥም የተሰጣቸው ሲሆን፣ በዚሁ መሠረት ‹‹ገዳ ኦላና›› በሚል አዲስ ሥም ይጠራሉ ነው የተባለው፡፡

ለብልጽግና አባሉ በምዕራብ ደቡብ ሸዋ አባ ገዳዎች በጊንጪ ከተማ ተሰጥቷል የተባለው አዲስ ሥም፣ ከአባታቸው ሥም ‹‹በላይ›› ከሚለው ትርጉም የተወሰደ እንደሆነ ነው የተሰማው፡፡

ይህንኑ ሂደት ተከትሎም የብልጽግና አባሉ በመጪው ምርጫ በሚወዳደሩበት አዲስ አበባ ከተማ በተሰቀለ ፖስተር ላይ ከቀደመው መጠሪያቸው በፊት አዲሱ ‹‹ዶክተር ገዳ ኦላና›› የሚለው ሥማቸው ሠፍሮ ታይቷል፡፡

ሞጋሳ የኦሮሞ ሕዝብ ከሚተዳደርበት የገዳ ሥርዓት ውስጡ ካሉ ተቋማት መካከል መሆኑ የሚነገር ሲሆን፣ በዚህ ሥርዐት ብሔረሰቡን የሚቀላለቀል ሰው ሥያሜ ከተሰጠው በኋላ ከብሔረሰቡ አባላት መካከል እንደ አንዱ እንደሚቆጠር ድርሳኖች ያመለክታሉ፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img